👉በትምህርት ስርዓቱ አካታለች ነው የተባለው።
ነሐሴ 12 ቀን 2017 (መናኸሪያ ሬዲዮ) በሰፊው የሐሰት መረጃ መስፋፋት በፈጠረው የዲጂታል ዘመን፣ ፊንላንድ የሐሰት መረጃዎችንና ፕሮፓጋንዳዎችን ለመቋቋም የሚያስችል አዲስ ስልት ተግባራዊ እያደረገች ነው ተብሏል።
አገሪቷ ከ2013 ዓ.ም ጀምሮ የሐሰት ዜናዎችን የመለየት ትምህርትን ከስድስት ዓመት ዕድሜ ጀምሮ በሁሉም ትምህርት ቤቶች ሥርዓተ ትምህርት ውስጥ በማካተት ግንባር ቀደም ሚና እየተጫወተች ነው ተብሏል።
ይህ እርምጃ ተማሪዎች ስለ ኦንላይን ይዘት በጥንቃቄ እንዲያስቡ እና የምንጭ ትንታኔ የማድረግ ክህሎት እንዲያዳብሩ ለመርዳት ያለመ ነው ተብሏል። ይህም ተማሪዎች በመረጃ የተደገፈ ውሳኔ እንዲወስኑ እና ለሐሰት መረጃ ተጋላጭ እንዳይሆኑ ያግዛቸዋል ነው የተባለው።
ፊንላንድ ይህን አቀራረብ ተግባራዊ ለማድረግ የወሰነችው ከፕሮፓጋንዳ ጋር ለረዥም ጊዜ ያላትን ልምድ በመንተራስ ነው ተብሏል። ይህ ስልት ተማሪዎችን ለዲጂታል ዘመን ተግዳሮቶች የሚያዘጋጅ ሲሆን፣ በመረጃ የተደገፈ ማኅበረሰብ ለመገንባት የሚያስችል መሠረት ይጥላል ተብሎም ይጠበቃል።
የቴሌግራም ቻናላችን ይቀላቀሉ 👉 https://t.me/menaharia_fm
ምላሽ ይስጡ