ነሐሴ 12 ቀን 2017 (መናኸሪያ ሬዲዮ)በአዲስ አበባ ከተማ እና በሸገር ከተማ የሚገኙ የጋራ መኖሪያ ቤቶች የኤሌክትሪክ ሀይል ተጠቃሚ ለማድረግ እየተሰራ መሆኑን የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ አገልግሎት ዋና ስራ አስፈጻሚ ኢንጂነር ጌቱ ገረመው የተጠናቀቀዉ በጀት ዓመት ሪፖርት ባቀረቡበት ወቅት ተናግረዋል።
በጋራ መኖሪያ ቤቶች አካባቢ ከሀይል አቅርቦት ጋር በተገናኘ ነዋሪዎች ተደጋጋሚ ቅሬታ ሲያነሱ ይታያል በተለይም በኮሪደር ልማት የተነሱ እና የሀይል አቅርቦት ያላገኙ ነዋሪዎች በተደጋጋሚ ለተቋሙ ጥያቄ እያቀረቡ መሆኑን ተቋሙ አስታውቋል።
ጉዳዩን በተመለከተ ማብራሪያ የሰጡት የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ አገልግሎት ዋና ስራ አስፈጻሚ ኢንጂነር ጌቱ ገረመው የቆጣሪ ክፍያ ከፍለው አሁንም የግል ቆጣሪ ያልገባላቸው ነዋሪዎች መኖራቸውን በመግለጽ ችግሩ በ2018 አ.ዓ ሩብ በጀት አመት እንደሚፈታ ተናግረዋል።
በብሎክ አንድ ቆጣሪ ሲጠቀሙ የነበሩ ነዋሪዎችን ጥያቄ በቀጣዮቹ ወራት ለመመለስ የኤሌትሪክ ገመድ ዝርጋታ እና ከሌሎች መሰረት ልማት ከሚያሟሉ አካላት ጋር በጋር እየተሰራ መሆኑን ዋና ስራ አስፈጻሚው ጨምረው ገልጸዋል።
በኮሪደር ልማቱ ተነስተው ወደ ጋራ መኖሪያ ቤት የገቡ ነዋሪዎች እና እስካሁን የሀይል አቅርቦት ተደራሽ ባልተደረገባቸው አካባቢዎች የሀይል አቅርቦት ተጠቃሚ እንደሚሆኑም ኢንጂነር ጌቱ ገረመው አረጋግጠዋል።
የቴሌግራም ቻናላችን ይቀላቀሉ 👉 https://t.me/menaharia_fm
ምላሽ ይስጡ