ነሐሴ 12 ቀን 2017 (መናኸሪያ ሬዲዮ) በ2017 በጀት ዓመት 12 ወራት ተቋሙ ተግባራዊ ባደረገው ዲጂታል የሙስና ተግባር መጠቆሚያ ሞባይል አፕሊኬሽን እና በሌሎች አማራጮች ከቀረቡ 147 ጥቆማዎች 92 አመራርና ሰራተኞች ጥፋተኛ መሆናቸው ተረጋግጦ እርምጃ የተወሰደ ሲሆን የቀሪዎቹ ሂደት ላይ ይገኛል ተብሏል።
ተቋሙ ተግባራዊ ባደረገው የሙስና ጥቆማ ማቅረቢያ እና በሌሎች አማራጮች በቀረቡት ጥቆማዎች መሰረት እርምጃ ከተወሰደባቸው ሰራተኞች መካከል 11 የፅሁፍ፣ 63 የደመወዝ፣ 4 ስንብት፣ 5 ከቦታ ማንሳት እንዲሁም 9 ነፃ የተባሉ በድምሩ በ92 አመራርና ሰራተኞች ላይ እርምጃ ተወስዷል ነው የተባለው።
ተግባራዊ በተደረገው የዲጂታል ሙስና ጥቆማ መቀበያ አፕልኬሽን እና በሌሎች አማራጮች 364 ጥቆማዎች ቀርበው በ311 ጥቆማዎችን ማጣራት ተችሏል ነው የተባለው።
በበጀት ዓመቱ የብልሹ አሰራር ጥቆማ ከቀረበባቸው የስራ ሂደቶች መካከል የአዲስ ኃይል ጥያቄ፣ ገንዘብ ስብሰባና ቆጣሪ ንባብ፣ የኃይል መቆራረጥና ጥገና፣ የሰው ሃብት አስተዳደር፣ ከንብረት አያያዝና አጠቃቀም፣የግዥ ሥራዎችና ሌሎች ልዩ ልዩ ጉዳዮች ይገኙበታል ተብሏል።
በ2017 ዓ.ም ብቻ የቀረቡ ጥቆማዎች ብዛት በባለፉት 3 ተከታታይ ዓመታት ከቀረቡት ጥቆማዎች በ38 በመቶ ያደገ ሲሆን ይህም የዲጂታል መተግበሪያው/Mobile App የፈጠረው አዎንታዊ ተፅዕኖ ወይም ምቹ ሁኔታን የሚያሳይ ነው ተብሏል።
የቴሌግራም ቻናላችን ይቀላቀሉ 👉 https://t.me/menaharia_fm
ምላሽ ይስጡ