👉አንድ የጀርመን ስራ ፈጣሪ ኩባንያ ለወደፊት ትንሳኤ ሲል የሰዎችን አስክሬን በማቀዝቀዝ ላይ ይገኛል ተብሏል
ነሐሴ 12 ቀን 2017 (መናኸሪያ ሬዲዮ) በበርሊን የሚገኘው ቶሞሮው ባዮ (Tomorrow Bio) የተሰኘው ኩባንያ በቅርቡ የሞቱ ሰዎችን በቀጣይ ዘመናት የሳይንስና ቴክኖሎጂ እድገት ወደ ህይወት ይመልሳቸዋል በሚል ተስፋ አስክሬናቸውን በማቀዝቀዝ ላይ መሆኑ ተዘግቧል።
ይህ አወዛጋቢ አገልግሎትም 200,000 ዶላር እንደሚያስከፍል ተገልጿል። ኩባንያው አስከሬኖቹ እንዳይበሰብሱ በፍጥነት እያቀዘቀዘ ነው ተብሏል።
ምንም እንኳን እስካሁን ድረስ በክራዮፕረዘርቬሽን(cryopreservation) የሰውን ልጅ ወደ ህይወት የመመለስ ሙከራ ያልተሳካ ቢሆንም፣ ኩባንያው ግን በርካታ ሰዎችን እና የቤት እንስሳትን አስክሬን አስቀድሞ ማቀዝቀዙ ተገልጿል።
ሌሎች 700 ሰዎች ደግሞ ለዚህ አገልግሎት ተመዝግበው እየተጠባበቁ ነው የተባለ ሲሆን ይህም በወደፊት የህክምና ግኝቶች ላይ ያላቸውን እምነት የሚያሳይ ነው ተብሏል።
ተቺዎች የአንጎል ጉዳት እና ሌሎች ችግሮች አስክሬኖቹን ወደ ህይወት መመለስ ከባድ ያደርጉታል ሲሉ እያስጠነቀቁ ቢሆንም የኩባንያው መስራቾች እነዚህን ችግሮች በባዮቴክኖሎጂ እና በተሃድሶ ህክምና (regenerative medicine) መፍታት እንደሚቻል እየተናገሩ ነው ተብሏል።
ይህ አገልግሎት የሞት ተፈጥሯዊነትን እና የሳይንስ ገደቦች ላይ ጥልቅ ጥያቄዎችን የሚያጭር ነው ተብሏል።
ሞት አንድ ቀን ጊዜያዊ ሊሆን ይችላል የሚለው ኩባንያው ለዚህ ጥያቄ መልስ ለመስጠት የቶሞሮው ባዮ ሙከራ የሳይንስ እና ተስፋ መጋ’ጫ መድረክ ሆኗል ነው የተባለው።
ቶሞሮው ባዮ ስለ ሞት እና የሁለተኛ ዕድል ያለንን አስተሳሰብ በመፈተን ላይ ይገኛል የተባለ ሲሆን ይህ ደፋር ሙከራ “የወደፊቱ የሕክምና መንገድ ሊሆን ይችላል ወይስ ሌላ የሰው ልጆች ሙከራ? “በሚል አሁንም በብዛት እያከራከረ ይገኛል።
የቴሌግራም ቻናላችን ይቀላቀሉ 👉 https://t.me/menaharia_fm
ምላሽ ይስጡ