ነሐሴ 12 ቀን 2017 (መናኸሪያ ሬዲዮ) የካናዳ አየር መንገድ(Air Canada)በአድማ ላይ ያሉ የበረራ አስተናጋጆች ወደ ስራ እንዲመለሱ የተሰጣቸውን ትዕዛዝ ባለመቀበላቸው የበረራ አገልግሎቱን ለመጀመር ያቀደውን ዕቅድ ለጊዜው ማገዱን አስታውቋል።
የአየር መንገዱ የበረራ አስተናጋጆች ማኅበር የኤር ካናዳን የበረራ አገልግሎት መልሶ የማስጀመር ውሳኔን በመቃወም አድማውን መቀጠላቸውን ገልጸዋል። ይህ በእንዲህ እንዳለ የካናዳ የሠራተኛ ግንኙነት ቦርድ አድማው ህገ-ወጥ ነው በማለት የሥራ ማቆም አድማውን እንዲያቆሙ ትዕዛዝ መስጠቱን ተከትሎ፣ የበረራ አስተናጋጆቹ ግን ይህንን ትዕዛዝ ባለመቀበላቸው ውጥረቱ ቀጥሏል ነው የተባለው።
በሁለቱም ወገኖች መካከል የነበረው ድርድር ባለመሳካቱ፣ አየር መንገዱ ዛሬ ሰኞ 170 በረራዎችን መሰረዙን አስታውቋል። ይህ ውሳኔ ከ10,000 በላይ ተጓዦችን እንደጎዳም ተገልጿል።
ኤር ካናዳ በሰጠው መግለጫ አድማው በአየር መንገዱ ላይ ከፍተኛ የገንዘብ ኪሳራ እያስከተለ እንደሆነ ገልጿል። አየር መንገዱ ወደፊት ስለሚወሰዱ እርምጃዎች በሚቀጥሉት ቀናት ለሕዝብ ይፋ እንደሚያደርግም አስታውቋል።
የቴሌግራም ቻናላችን ይቀላቀሉ 👉 https://t.me/menaharia_fm
ምላሽ ይስጡ