ነሐሴ 07 ቀን 2017 (መናኸሪያ ሬዲዮ) የፖፕ ንጉስ በመባል የሚታወቀው የሟቹ ታዋቂ አርቲስት ማይክል ጃክሰን በ1997ቱ የሂስትሪ ወርልድ ቱር (HIStory World Tour) ኮንሰርት ወቅት ተለብሶ የነበረው እና በአልማዝ መሰል ድንጋዮች ያጌጠ ካልሲ በፈረንሳይ በኒም ከተማ በተካሄደ ጨረታ ላይ ወደ $9,000 በሚጠጋ ዋጋ መሸጡ ታውቋል።
ከአርቲስቱ ሞት በኋላም ቢሆን ለግል ንብረቶቹ ያለው ከፍተኛ ፍላጎት መቀጠሉን የሚያሳይ ይህ ክስተት፣ ካልሲው “ቢሊ ጂን” (Billie Jean) የተባለውን ዘፈን ሲያቀርብ የለበሰው እንደነበር ተገልጿል።
ምላሽ ይስጡ