ነሐሴ 08 ቀን 2017 (መናኸሪያ ሬዲዮ) ዋትስአፕ (WhatsApp) የተሰኘው የመልዕክት መላላኪያ መተግበሪያ ሩሲያ አገልግሎቱን ለማገድ እየሞከረች መሆኑን አስታውቋል። ኩባንያው እንደገለጸው፣ ሩሲያ ይህን የምታደርገው መድረኩ ለተጠቃሚዎች ደህንነቱ የተጠበቀ ግንኙነት የማድረግ መብት ስለሚሰጥ ነው ብሏል፡፡
ሩሲያ በበኩሏ የውጭ ኩባንያዎች የሆኑት ዋትስአፕ እና ቴሌግራም በወንጀል እና በሽብርተኝነት ጉዳዮች ላይ ከህግ አስከባሪ አካላት ጋር መረጃ ለመለዋወጥ ፈቃደኛ ባለመሆናቸው፣ በጥሪ አገልግሎታቸው ላይ ገደብ መጣል መጀመሯን ገልጻለች።
ዋትስአፕ በሰጠው መግለጫ፣ “ዋትስአፕ የግል፣ ከጫፍ እስከ ጫፍ በምስጠራ የተጠበቀ (end-to-end encrypted) ነው፣ እናም የመንግስትን ደህንነቱ የተጠበቀ ግንኙነት የማድረግ መብት የመጣስ ሙከራዎችን ይቃወማል። ሩሲያ ከ100 ሚሊዮን በላይ ለሚሆኑ የሩሲያ ህዝቦች አገልግሎቱን ለማገድ እየሞከረች ያለውም ለዚህ ነው” ብሏል። “በሩሲያ ውስጥ ጨምሮ በየትኛውም ቦታ ያሉ ሰዎች ደህንነቱ የተጠበቀ ግንኙነት እንዲያገኙ የተቻለንን ሁሉ ማድረጋችንን እንቀጥላለን” ሲልም አክሏል።
ይህ ውጥረት የተፈጠረው ሩሲያ “ሉዓላዊ ኢንተርኔት” ለመፍጠር በምታደርገው ጥረት አካል ነው ተብሏል። ባለስልጣናት የውጭ አገልግሎቶችን በአገር ውስጥ በሚሰሩ መተግበሪያዎች ለመተካት እየሞከሩ መሆኑ ተመላክቶ ይህም የመንግስት ቁጥጥርን ለማጠናከር ያለመ እንደሆነ ተነግሯል።
ምላሽ ይስጡ