ነሐሴ 08 ቀን 2017 (መናኸሪያ ሬዲዮ) በሀገሪቱ በተለያዩ አካባቢዎች ካሉ የታጣቂ ቡድኖች ሰላም ፈልገው እጅ የሰጡ ግለሰቦችን ወደ ብሄራዊ የታሃድሶ ኮሚሽን እንዲገቡ በማድረግ ስልጠና አግኝተው ማህበረሰቡን እንዲቀላቀሉ የማድረግ ስራ መጀመሩ ይታወሳል፡፡
በዚህም ኮሚሽኑ ወደ ስልጠና መግባት የሚፈልጉ በተለያዩ ክልሎች የሚገኙ የቀድሞ ታጣቂዎችን በመመዝገብ ትጥቃቸውን አስረክበው ስልጠና እንዲወስዱ ማድረጉን የብሄራዊ ተሃድሶ ኮሚሽን የኮሚዩኒኬሽን ሃላፊ አቶ ሃብታሙ መለሰ ለጣቢያችን ገልፀዋል፡፡
እስካሁን በዚህ ሂደት ከትግራይ ክልል ከ54ሺህ በላይ፤ ከአማራ 5ሺህ በላይ፣ ከኦሮሚያ ከ5 ሺህ 300 በላይ እንዲሁም ከአፋር ከ1ሺህ 700 በላይ የሚሆኑ የቀድሞ ታጣቂዎች በድምሩ ከ66 ሺህ በላይ የሚሆኑት ሰልጥነው ማህበረሰቡን መቀላቀላቸውን ተናግረዋል፡፡
በስልጠናውም ከስነልቦና ድጋፍ ጀምሮ ሰላማዊ በሆነ መንገድ ህይወታቸውን መምራት የሚችሉበትን እና የግብረ ገብ ስልጠና ማግኘታቸውን አስታውቀዋል፡፡
ኮሚሽኑ አሁንም ባሉት 3 ማዕከላት ከተለያዩ አካባቢዎች በየቀኑ በእያንዳንዱ ማዕከል 200 የቀድሞ ታጣቂዎችን እየተቀበለ መሆኑን የብሄራዊ ተሃድሶ ኮሚሽን የኮሚዩኒኬሽን ሃላፊ አቶ ሃብታሙ መለሰ ገልፀዋል፡፡
ከዚህ ቀደም በሚፈለገው ልክ ከፍተኛ ቁጥር ያላቸው ሰልጣኞችን ለመቀበል የበጀት እጥረት እንደነበረ በመጥቀስ አሁን ላይ የተለያዩ ለጋሽ ድርጅቶች መኖራቸውን እንዲሁም ከተለያዩ ሀገራት ድጋፍ የማሰባሰብ ስራ እያከናወኑ እንደሚገኙ ጠቅሰዋል፡፡
ማህበረሰቡም ወደየ አካባቢያቸው ሲመለሱ መልካም አቀባበል በማድረግ ሰለማዊ ህይወት እንዲመሩ በማድረግ የበኩሉን ሃላፊነት እንዲወጣ እንዲሁም ወደ ሰላማዊ ህይወት መመለስ የሚፈልጉ ታጣቂዎች ትጥቃቸውን አስረክበው ወደ ስልጠና ማዕከላቱ እንዲገቡ አቶ ሃብታሙ ጥሪያቸውን አቅርበዋል፡፡
የቴሌግራም ቻናላችን ይቀላቀሉ 👉 https://t.me/menaharia_fm
__
ሀሳብ እና’ሳ’ፍራለን 📞
👉011-639-28-52
👉011-639-37-63
ምላሽ ይስጡ