ነሐሴ 01 ቀን 2017(መናኸሪያ ሬዲዮ)በመርሀ ግብሩ ላይ ጥሪ የተደረገላቸው አካላት የተገኙ ሲሆን የኢፌዴሪ ፕሬዝዳንት ታዬ አጽቀስላሴ፤ የጤና ሚኒስትር ዶክተር መቅደስ ዳባን ጨምሮ ከቻይና ሀገርም ጥሪ የተደረገላቸው እንግዶች ተገኝተዋል፡፡
በዛሬው ዕለት እየተካሄደ ባለው መርሀ ግብርም ቻይና እና ኢትዮጵያ የረጅም ጊዜ ግንኙት እንዳላቸው የተገለፀ ሲሆን በዚህም አሁን ባለንበት የክረምት ወቅት መሆኑን ተከትሎ ዜጎች የክረምት የበጎ ፈቃድ አገልግሎት ማግኘት የሚችሉበት እና ተጠቃሚ የሚሆኑበት ሁኔታ ተፈጥሯልም ነው የተባለው።
መርሀ ግብሩ ከቻይና በሚመጡ እና ከ40 የሚበልጡ ባለሙያዎች ተሳታፊ ያደረገ ሲሆን በተለያዩ የህክምና ዘርፎች ላይ ተሳትፎዓቸውን ማሳየት እንደሚችሉ ነው የተገለጸው ።
በሚሰጠው የክረምት በጎ ፈቃድም አገልግሎት ከሚገኙ ባለሙያዎች ውስጥም የአንጎል፣የአይን፣የህፃናት ልብ ቀዶ ጥገና እና ህክምና፣የማህፀን እና ፅንስ ህክምና እስፔሻሊት ይገኙበታልም ነው የተባለው።
በተያያዘም የጤና ሚኒስቴር ዶክተር መቅደስ ዳባ የሁለቱ ሀገራት ግንኙነትን በይበልጥ የሚያስተሳስር እና የሚበረታታ ነው ብለዋል።
በባለፈው የክረምት ወቅት 4 ሚሊየን የሚሆኑ ዜጎችን የክረምት የበጎ ፈቃድ ህክምና ተጠቃሚ ማድረግ እንደተቻለ እና ቁጥሩንም ወደ 5 ሚሊየን ለማሳደግ እየተሰራ ይገኛል ብለው፤በገጠር እና በከተማ የሚኖሩ ዜጎችንም ተጠቃሚ አድርጓልም ነው ያሉት። ህክምናው እስከ ጳጉሜ 5/2017 እንሚቆይ ተገልጿል፡፡
ምላሽ ይስጡ