ሐምሌ 29 ቀን 2017(መናኸሪያ ሬዲዮ) በሰሜን ታንዛኒያ የሚገኘው የናይትሮን ሐይቅ፣ እንስሳትን ወደ ድንጋይነት የመቀየር ኃይል ያለው አስገራሚና ገዳይ የውሃ አካል እንደሆነ ተዘግቧል።
ይህ አስፈሪ ክስተት የሚፈጠረው ሐይቁ እጅግ በጣም ከፍተኛ የሆነ የአሲዳማነት መጠን ስላለው ሲሆን፣ የአሲዳማነት መጠኑ እስከ 10.5 በመቶ ይደርሳል የተባለ ሲሆን ይህም የሰውነት አካላትን በጣም የሚያቃጥል መሆኑ ተመላክቷል።
ሐይቁ በአካባቢው ከሚገኙ እሳተ ገሞራዎች አመድ በወጡ የማዕድን ጨውች የበለጸገ ነው ተብሏል።
በተለይም ከፍተኛ መጠን ያለው ሶዲየም ካርቦኔት የያዘ ሲሆን፣ እነዚህ ኬሚካላዊ ውህዶች የሞቱ እንስሳትን አካል በማጠንከር “ወደ ድንጋይነት ተቀየሩ” የሚል አስፈሪ ቅዠት እንዲፈጥሩ ያደርጋል ተብሏል።
በሐይቁ ውስጥ ያለው የሙቀት መጠን እስከ 60°ሴ ሊደርስ እንደሚችል የተጠቆመ ሲሆን፣ ይህ ከፍተኛ ሙቀትና የውሃ ትነት የማዕድናቱን መጠን የበለጠ እንዲጨምር ያደርገዋል ተብሏል።
ይህ ሁሉ አስቸጋሪ ሁኔታ ቢኖርም፣ ናይትሮን ሐይቅ ሙሉ በሙሉ ሕይወት አልባ አይደለም የተባለ ሲሆን አንዳንድ እጅግ በጣም ከባድ በሆኑ አካባቢዎች ውስጥ የሚኖሩ ፍጥረታት በውሃው ውስጥ የሚኖሩ ሲሆን፣ ሐይቁ ለጥቂት የፍላሚንጎ ዝርያዎች ብቸኛው የመራቢያ ስፍራ እንደሆነ የናሽናል ጆግራፊ እና የታንዛኒያ ቱሪስት ቦርድ መረጃ ያመላክታል።
ነገር ግን ለአብዛኞቹ እንስሳት፣ ወደ ሐይቁ መቅረብ ለሞት የሚያበቃ ሲሆን፣ የሐይቁ እንግዳ ገጽታ እና የገዳይነት ችሎታው ከምድር አስፈሪ ድንቆች መካከል አንዱ እንዲሆን አድርጎታል ነው የተባለው።
የቴሌግራም ቻናላችን ይቀላቀሉ 👉 https://t.me/menaharia_fm
__
ሀሳብ እና’ሳ’ፍራለን 📞
👉011-639-28-52
👉011-639-37-63
ምላሽ ይስጡ