👉ነጻነትን የማግኘት ሙከራ ሰብዓዊ መብት ነው ተብሏል
ሐምሌ 29 ቀን 2017(መናኸሪያ ሬዲዮ)የጀርመን የፍትህ ስርዓት በአንድ አስገራሚና ልዩ ህግ ይታወቃል የተባለ ሲሆን ይኸውም አንድ እስረኛ ከእስር ቤት ለማምለጥ ቢሞክርም ሆነ ቢያመልጥ በድርጊቱ ብቻ ለተጨማሪ ቅጣት አይዳረግም ተብሏል፡፡
ይህ መርህ በጀርመን የወንጀል ህግ ውስጥ የተካተተ ሲሆን፣ የአንድ ሰው ነፃነትን የማግኘት ፍላጎት ተፈጥሯዊና ሰብአዊ መብት ነው በሚል መሰረታዊ ፍልስፍና ላይ የተመሰረተ መሆኑ ተመላክቷል።
የጀርመን ህግ አውጪዎች አንድ ሰው በግዞት ወይም በእስር ውስጥ መሆኑ በራሱ የነጻነት ጥማቱን አያጠፋውም ብለው እንደሚምኑ የተመላከተ ሲሆን አንድ ግለሰብ ከእስር ለመሸሽ የሚያደርገው ሙከራ የህግ ግዴታውን የጣሰ ቢሆንም፣ በራሱ እንደ ተጨማሪ የወንጀል ድርጊት ሊፈረጅ እንደማይገባ የፍትህ ስርዓቱ አምኖበታል ነው የተባለው፡፡
ይህ ህግ ሙሉ በሙሉ ከቅጣት ነጻ ያደርጋል ማለት ግን አይደለም የተባለ ሲሆን ከእስር የማምለጡ ድርጊት በራሱ ወንጀል ባይሆንም፣ እስረኛው ሲያመልጥ የፈጸማቸው ተጓዳኝ ወንጀሎች ካሉ ለነዚያ ቅጣት ይጣልበታል ተብሏል፡፡
ለምሳሌ ያክልም ለማምለጥ ሲሞክር የንብረት ውድመት፤የአካል ጉዳት ማድረስ፤ከእስር ለማምለጥ ሌሎች ሰዎች እንዲረዱት ካደረገ እንዲሁም በማምለጫው ወቅት የጦር መሳሪያ ከተጠቀመ ከማምለጡ ሂደት ውጪ በሌሎች ወንጀሎች ተጠያቂ ይሆናል ተብሏል፡፡
እንደ አጠቃላይ ህጉ የሚያተኩረው “ነጻነትን መፈለግ ወንጀል አይደለም” በሚለው ሃሳብ ላይ መሆኑ የተመላከተ ሲሆን ፣ ይህንን ህጋዊ መብት በመተግበር ሂደት ውስጥ ሌሎች ሰዎች ላይ ጉዳት ማድረስ ወይም ንብረት ማውደም ግን በምንም መልኩ አይታገስም ተብሏል።
ይህ ልዩ የጀርመን ህግ በዓለም አቀፍ ደረጃ ብዙ የህግ ባለሙያዎችና የማህበራዊ ሳይንስ ሊቃውንት የክርክር ርዕስ ሆኗል። አንዳንዶች “የሰው ልጅ ነጻነትን የማግኘት ተፈጥሮአዊ ግዴታውን ማክበር ነው” ሲሉ ሲከራከሩ፣ ሌሎች ደግሞ “የወንጀል ፍትህ ስርዓትን የሚያዳክም እና ስርዓትን የሚጥስ ነው” በማለት እንደሚተቹት ከጀርመን የወንጀል ህግ የተገኘው መረጃ አመላክቷል።
የቴሌግራም ቻናላችን ይቀላቀሉ 👉 https://t.me/menaharia_fm
__
ሀሳብ እና’ሳ’ፍራለን 📞
👉011-639-28-52
👉011-639-37-63
ምላሽ ይስጡ