👉የቋንቋ አለመቻል ችግርን ይቀርፋል ተብሏል
ሐምሌ 27 ቀን2017(መናኸሪያ ሬዲዮ)በአንድ አፍሪካዊ የፈጠራ ባለሙያ የተሰራው አዲስ የጆሮ ማዳመጫ፣ ከ40 በላይ የሚሆኑ ቋንቋዎችን የበይነመረብ ግንኙነት ሳያስፈልገው በቅጽበት መተርጎም እንደሚችል ተገለጸ።
የፈጠራ ውጤቱ በዓለም አቀፍ ደረጃ ትኩረት አግኝቷል።
የዚህ አብዮታዊ ቴክኖሎጂ ፈጣሪ፣ ጋናዊው ሥራ ፈጣሪ እና የቴክኖሎጂ ባለሙያ ዳኒ ማኑ (Danny Manu) የተባለ ግለሰብ ነው ተብሏል።
ግለሰቡ ይህንን የጆሮ ማዳመጫ የፈጠረው በዓለም ላይ ያሉ የቋንቋ እንቅፋቶችን ለማስወገድ እና በሰዎች መካከል ያለውን ግንኙነት ለማቀላጠፍ በሚል ዓላማ ነው ተብሏል።
የጆሮ ማዳመጫው “Mymanu CLIK” ተብሎ የሚጠራ ሲሆን፣ በጉዞ፣ በንግድ እና በዓለም አቀፍ ኮንፈረንሶች ላይ ትልቅ ለውጥ እንደሚያመጣ ይጠበቃል ተብሏል።
አብዛኛዎቹ የትርጉም መሣሪያዎች የኢንተርኔት ግንኙነትን የሚጠይቁ ሲሆን፣ የዳኒ ማኑ ፈጠራ ግን ያለ ምንም ግንኙነት መስራት መቻሉ ትልቅ ለየት ያለ ያደርገዋል ነው የተባለው።
ይህ የፈጠራ ውጤት አፍሪካ በቴክኖሎጂ ዘርፍ ያላትን እምቅ አቅም የሚያሳይ ነው ተብሏል።
የቴሌግራም ቻናላችን ይቀላቀሉ 👉 https://t.me/menaharia_fm
ምላሽ ይስጡ