ሐምሌ 28 ቀን 2017(መናኸሪያ ሬዲዮ)በጃፓን የባቡር ትራንስፖርት አገልግሎት ሰጪ ድርጅቶች ሰዓት አክባሪነትን ምን ያህል እንደሚያስከብሩ የሚያሳይ አንድ ያልተለመደ ክስተት ተመዝግቧል።
ከቅርብ ጊዜ ወዲህ በባቡር ተሳፋሪዎች ዘንድ መነጋገሪያ የሆነው ይህ ክስተት፣ አንድ የባቡር ሹፌር ባቡሩ ለታቀደለት ሰዓት የደረሰው በ35 ሰከንድ ዘግይቶ በመሆኑ ብቻ ይቅርታ መጠየቁን ያመለክታል።
የባቡሩ ሹፌር ይቅርታ መጠየቁ ብቻ ሳይሆን፣ ይህንንም ተከትሎ ባቡሩ ውስጥ የነበሩ ሁሉም ተሳፋሪዎች ለጉዞአቸው የከፈሉትን ሙሉ ገንዘብ ተመላሽ እንዲደረግላቸው መደረጉን መረጃዎች ያሳያሉ።
ይህ ክስተት የጃፓንን የህዝብ ትራንስፖርት ዘርፍ የላቀ ትክክለኛነት፣ የኃላፊነት ስሜት እና ለደንበኞች ያላቸውን ከፍተኛ ግምት የሚያሳይ ነው ተብሏል። እንደ ብዙ ሀገራት ሁሉ ለበርካታ ሰዓታት መዘግየት እንኳን እንደተለመደ ነገር የሚታይበት ሁኔታ ሳይሆን፣ በጃፓን እያንዳንዱ ሰከንድ የራሱ ዋጋ እንዳለው ይህ ክስተት በተጨባጭ አስረድቷል ተብሏል።
የጃፓን የባቡር ኩባንያዎች ይህን የመሰለ አስደናቂ የደንበኛ አገልግሎት በመስጠት በዓለም ዙሪያ አድናቆትን እያተረፉ ይገኛሉ።
የቴሌግራም ቻናላችን ይቀላቀሉ 👉 https://t.me/menaharia_fm
ምላሽ ይስጡ