ሐምሌ 24 ቀን 2017(መናኸሪያ ሬዲዮ)የቀድሞ የቅዱስ ጊዮርጊስ እና የኢትዮጵያ ብሄራዊ ቡድን የአጥቂ መስመር ተጫዋች የሆነው ሙሉጌታ ከበደን የሚዘክር ኮሚቴ በዛሬው እለት በቤሌቪው ሆቴል መግለጫ ሰጥተዋል።
ኢንስትራክተር ሰውነት ቢሻው ፤ አሰልጣኝ ስዩም እንዲሁም የኦሎምፒክ ኮሚቴ የቴክኒክ ክፍል እና ህዝብ ግንኙነት ሀላፊ አቶ ቢልልኝ መቆያ በጋራ በመሆን ስለተቋቋመው ኮሚቴ ማብራሪያ ሰጥተዋል።
የቀድሞው የኢትዮጵያ ብሔራዊ ቡድን እና የቅዱስ ጊዮርጊስ አጥቂ ሙሉጌታ ከበደ የኢትዮጵያ ኮከብ ተጫዋች ሲሆን በ13 ዓመታት የእግርኳስ ቆይታው አቋሙ ሳይዋዥቅ ፣ በድንቅ ብቃቱ የሚታወስ ሲሆን በደጋፊዎችና በእግር ኳስ አፍቃሪያን የሚወደድ ተጫዋች መሆኑ የሚታወስ ነው።
ወለዬው በሚል ቅጽል ስሙ የሚታወቀው ሙሉጌታ ከበደ በአጋጠመው የጤና እክል በሕክመና ሲረዳ ቆይቶ ትላንትና ሕይወቱ አልፏል፡፡
ትውልዱ በደቡብ ወሎ ዞን ለገሂዳ ወረዳ መሆኑን የሚያስረዳው የሙሉጌታ ተስፋዬ የሕይወት ታሪክ በአጭሩ በአሰልጣኝ ስዩም ቀርቧል።
ኮሚቴው ከተቋቋመ 2 ወር መሆኑ የተገለፀ ሲሆን ዋና አላማው ሙሉጌታ ከበደ ብሄራዊ ጀግና የሆነ የሀገር ውለታ ከመሆኑ ጋር በተያያዘ ስራውን ለተተኪ ትውልድ ማስተላለፍ መሆኑን አሳውቀዋል።
በቀጣይ የሙሉጌታ ከበደ ፋውንዴሽን ለማቋቋም ስሪዎችን መስራት ፤ ከመንግስታዊ እና መንግስታዊ ካልሆኑ ተቋማት ጋር በጋራ በመሆን በስሙ አደባባይ እንዲሰየም ለማድረግ ፤ ታሪኩ እና ገድሉን የሚዘክር ፊልም እንዲሁም መጽሀፍ እንዲታተም ማድረግ ፤ በስሙ አመታዊ የዋንጫ ውድድር እንዲዘጋጅ ማድረግ እና አመታዊ ሙሉጌታ ከበደ የሚል የሽልማት ዘርፍ በማዘጋጀት ጥሩ አቅም ያላቸውን የእግርኳስ ተጫዋቾች የሚሸለሙበትን መድረክ ማዘጋጀት ፤ የሙሉጌታ ከበደ ፊውንዴሽን ለመቋቋም የሚያስችል መሰረት መጣል መሆኑን አሳውቀዋል።
ኢንስትራክተር ሰውነት ቢሻው በበኩላቸው ጀግኖችን መዘከር መለመድ ያለበት መሆኑ እና ሚድያዎችም ከዜና ግብአት በዘለለ ትኩረት አድርገው እንዲሰሩበት አፆንኦት ሰጥተዋል።
አቶ ቢልልኝ መቆያ በበኩላቸው ለሙሉጌታ ብቻ የተቋቋመ ኮሚቴ ሳይሆን መንግስቱ ወርቁንም ሌሎች ጀግኖችንም ሁሌም መዘከር አለባቸው የሚል አላማ ያነገበ መሆኑን አሳውቀዋል።
አያይዘው በባህርዳር ስቴዲየም የመጀመሪያ መግቢያ በር አቶ ይድነቃቸው ተሰማ የሚል ስያሜ ተሰጥቶታል ስለዚህ በመዲናችን አዲስ አበባም ሊሆን ይችላል በተለያዩ ስቴዲየሞችም ለሙሉጌታ ከበደ ስያሜ እንዲሰጠው ማድረግ እንደሚቻል ተናግረዋል።
ሙሉጌታ ከበደ ከጊዜው የቀደመ የሚባል አይነት ክህሎት እና አቅም ያቀረበው ተጫዋች ሲሆን በእግርኳስ ህይወቱ 7 የኢትዮጵያ ሻምፒዮና ፤ 6 ጊዜ የአሸናፊዎች አሸናፊ ዋንጫ ማሳካት ችሏል።
በቅዱስ ጊዮርጊስ በነበረው ቆይታ 3 ጊዜ ኮኮብ ጎል አግቢ ፤ 3 ጊዜ ኮኮብ ተጫዋች ሆኖ ያጠናቀቀ ተጫዋችም ነበር።
ዝክረ ሙሉጌታ ከበደ አስተባባሪ ኮሚቴ በቀጣይ ተቋማዊ ለማችረግ እንደሚሰራ እና ሌሎች ለሀገራቸው ብዙ ውለታ የዋሉ ጀግና ግለሰቦችን ዘመን ተሻጋሪ ስሪዎቻቸው ለትውልድ እንዲተላለፍ ለማድረግ ጥረት የሚያደርግ ሲሆን ይሄ ኮሚቴ ዘለቄታዊነቱ እንዲረጋገጥ የሚመለከታቸው አካላት የበኩላቸውን ሚና እንዲወጡ ጥሪ ቀርቧል።
__
ሀሳብ እና’ሳ’ፍራለን 📞
👉011-639-28-52
👉011-639-37-63
ምላሽ ይስጡ