ሐምሌ 23 ቀን 2017(መናኸሪያ ሬዲዮ)የአዲስ አበባ ከተማ ንግድ ቢሮ ከ70 ግራም በታች ደቦ ሲሸጡ የተገኙ 114 ዳቦ ቤቶች ላይ እስከ ማሸግ የደረሰ እርምጃ መውሰዱን አስታውቋል፡፡
የቢሮው ኢንስፔክሽን እና ሬጉላቶሪ ዳይሬክተር አቶ ዮሴፍ አሰፋ በተጠናቀቀው በጀት አመት 20ሺህ 5መቶ 35 በሚሆኑ የዳቦ ቤቶች ላይ በተደረገው ክትትል ወደ 114 የሚደርሱት ከተቀመጠው የግራም መጠን በታች ሲሸጡ ተገኝተዋል ብለዋል፡፡
አቶ ዮሴፍ በቅድሚያ የቃል እና የጽሁፍ ማስጠንቀቂያ ለንግድ ተቋማቱ እንደተሰጠ ገልጸው ሳያስተካክሉ የቀሩት ላይ እስከ ማሸግ የሚደርስ እርምጃ እንደተወሰደባቸው ተናግረዋል፡፡ የተሰጣቸውን ማስጠንቀቂያ በፍጥነት በማሻሻል ወደ መደበኛ ግራም መልሰው የሸጡ ዳቦ ቤቶች መኖራቸውን የተናገሩት ዳይሬክተሩ ሸማቹ ማህበረሰብ በራሱ የቁጥጥሩ አካል በመሆን ከግራም በታች የሚሸጡ ዳቦ ቤቶችን እንዲጠቁም ጥሪ አቅርበዋል፡፡
በዳቦ መሸጫ ቤቶች ላይ የግራም መጠን እንዲለጥፉ መደረጉን ተከትሎ ሸማቹ ህብረተሰብ ከተፈቀደው ግራም በታች የሚሸጡ ነጋዴዎችን በ85 88 የነጻ የሰልክ መስመር በመደወል ጥቆማ ቢሰጡ፤ ለቁጥጥር ስራው በግብዓትነት እንደሚያግዝ አቶ ዮሴፍ አመላክተዋል።
__
ሀሳብ እና’ሳ’ፍራለን 📞
👉011-639-28-52
👉011-639-37-63
ምላሽ ይስጡ