ሐምሌ 23 ቀን 2017(መናኸሪያ ሬዲዮ)የአውስትራሊያ መንግስት ከ16 ዓመት በታች የሆኑ ህጻናት ዩቲዩብ አካውንት እንዳይኖራቸው የሚያግድ አዲስ ህግ ይፋ አድርጓል። ይህ ውሳኔ ከዚህ ቀደም ዩቲዩብን ከእንደዚህ አይነቱ እገዳ ነፃ የማድረግ አቋሙን የቀየረ ነው ተብሏል። ህጉ ታህሳስ ወር ላይ ጀምሮ ተግባራዊ መሆኑ ተገልጾ፣ የዩቲዩብን ጨምሮ የማህበራዊ ሚዲያ መድረኮች ይህንን ህግ ባለማክበራቸው እስከ 49.5 ሚሊዮን የአውስትራሊያ ዶላር (33 ሚሊዮን የአሜሪካ ዶላር) ቅጣት ሊጣልባቸው ይችላል ተብሏል።
የአውስትራሊያ ጠቅላይ ሚኒስትር አንቶኒ አልባኒዝ እና የኮሙዩኒኬሽን ሚኒስትር አኒካ ዌልስ እንደተናገሩት፣ ይህ እርምጃ የተወሰደው የማህበራዊ ሚዲያ በልጆች ላይ የሚያደርሰውን አሉታዊ ተፅዕኖ ለመቀነስ ነው ብለዋል።
በአዲሱ ህግ መሰረት፣ ከ16 ዓመት በታች የሆኑ ህጻናት የዩቲዩብ አካውንት መክፈት ባይችሉም፣ ያለ አካውንት ቪዲዮዎችን ማየት ወይም በወላጆቻቸው ቁጥጥር ስር መጠቀም ይችላሉ ተብሏል። ከዩቲዩብ በተጨማሪ ፌስቡክ፣ ኢንስታግራም፣ ስናፕቻት፣ ቲኪቶክ እና ኤክስ (ትዊተር) ከ16 ዓመት በታች ለሆኑ ታዳጊዎች የታገዱ የማህበራዊ ሚዲያ መድረኮች ዝርዝር ውስጥ ይገኛሉ ነው የተባለው።
አውስትራሊያ በዓለም አቀፍ ደረጃ ህጻናትን ከማህበራዊ ሚዲያ ለመጠበቅ የምታደርገውን ጥረት በተባበሩት መንግስታት ድርጅት መድረኮች ላይ እንደምታስተዋውቅ ተመላክቷል፡፡
ይህ የሚያሳየው የማህበራዊ ሚዲያ በወጣቶች ላይ የሚያደርሰውን ተፅዕኖ በተመለከተ ዓለም አቀፍ ስጋት እየጨመረ መምጣቱን መሆኑ ተመላክቷል፡፡
__
ሀሳብ እና’ሳ’ፍራለን 📞
👉011-639-28-52
👉011-639-37-63
ምላሽ ይስጡ