ሐምሌ 23 ቀን 2017(መናኸሪያ ሬዲዮ)አንድ ስሙ ያልተጠቀሰ የቻይና ኩባንያ በሰከንድ እስከ 30 ትንኞችን ወይም ቢንቢዎችን መግደል የሚችል አዲስ የሌዘር መሣሪያ መሥራቱን ይፋ አደረገ።
ይህ ቴክኖሎጂ በቢንቢዎች አማካኝነት የሚተላለፉ በሽታዎችን ለመከላከል ትልቅ አስተዋፅኦ ያደርጋል ተብሏል።
መሣሪያው ብንቢዎችን ለመለየት የላቀ የቪዥን ቴክኖሎጂን እንደሚጠቀም ተገልጿል። አንዴ ከተገኙ በኋላ ኃይለኛ የሌዘር ጨረር በመጠቀም በቅጽበት ይገድላቸዋል ነው የተባለው።
ኩባንያው ይህ መሣሪያ ለአካባቢ ተስማሚ የሆነ የቢንቢ መቆጣጠሪያ ዘዴ እንደሆነ ገልጿል።
ይህ ቴክኖሎጂ በተለይ እንደ ወባ፣ ዴንጊ እና ዚካ ባሉ በትንኞችና በቢንቢዎች በሚተላለፉ በሽታዎች ለሚሰቃዩ አካባቢዎች ትልቅ እፎይታ ሊሆን እንደሚችል ባለሙያዎች ይገልጻሉ።
መሣሪያው በውጪም ሆነ በቤት ውስጥ አገልግሎት እንዲውል ተደርጎ የተሠራ ሲሆን፣ ለሰዎች እና ለሌሎች እንስሳት ምንም ጉዳት የሌለው መሆኑ ተረጋግጧል።
ኩባንያው በቀጣይነት የመሣሪያውን አቅም ለማሻሻል እና በዓለም ዙሪያ ለገበያ ለማቅረብ እቅድ እንዳለው አስታውቋል።
ይህ አዲስ የቴክኖሎጂ ግኝት የህብረተሰብ ጤናን በማሻሻል ረገድ ትልቅ ተስፋን መያዙን እየተዘገበ ነው።
ምላሽ ይስጡ