👉በዓለም የመጀመሪያው የተሳካ የብልት ንቅለ ተከላ ከተደረገ ከስድስት ወራት በኋላ አንድ ጤናማ ሕፃን መወለዱ ተዘግቧል
ሐምሌ 22 ቀን 2017(መናኸሪያ ሬዲዮ) በደቡብ አፍሪካ የተደረገው ይህ አስደናቂ የሕክምና ስኬት ከብዙ ዓመታት ምርምር እና ትጋት በኋላ እውን ሆኗል የተባለ ሲሆን ቀዶ ሕክምናው የተደረገለት የ21 ዓመቱ ወጣት ታካሚ፤ ብልቱን ያጣው በባህላዊ ግርዛት ሥነ ሥርዓት ወቅት በደረሰበት ከፍተኛ ጉዳት እንደነበር ተገልጿል።
በዚህም በስቴለንቦሽ ዩኒቨርሲቲ እና በታይገርበርግ ሆስፒታል የሚገኝ የቀዶ ህክምና ቡድን ለ9 ሰዓታት የፈጀ ውስብስብ ቀዶ ህክምና በተሳካ ሁኔታ እንዳጠናቀቀ ተገልጾ፤ ከሶስት ወራት ባልበለጠ ጊዜ ውስጥ ታካሚው ሙሉ የሽንት እና የወሲብ ተግባራቱን መመለስ የቻለ ሲሆን፣ ከዚያ ብዙም ሳይቆይ ደግሞ ጤናማ ሕፃን ተቀብሏል ነው የተባለው።
የሕክምና ቡድኑ ይህን ውስብስብ ቀዶ ሕክምና በማካሄድ ወደር የማይገኝለት ብቃት እና ቁርጠኝነት አሳይቷል ተብሏል፡፡ንቅለ ተከላው ከተሳካ በኋላ ታካሚው በጥሩ ሁኔታ እያገገመ እንደነበረ የተገለጸ ሲሆን፣ ከስድስት ወራት በኋላ የሕፃን መወለድ ዜና ደግሞ የሕክምናውን ሙሉ ስኬት በድጋሚ አረጋግጧል ነው የተባለው፡፡
ይህ ክስተት የመራቢያ ጤና ችግር ላለባቸው ወንዶች ታላቅ ተስፋ የሚሰጥ ነው የተባለ ሲሆን የዚህ ዓይነቱ ንቅለ ተከላ ስኬት የሕክምና ሳይንስ ድንበሮችን እንደገፋ የሚያሳይ ሲሆን፣ ወደፊትም ተመሳሳይ ችግር ላለባቸው ሰዎች ዘላቂ መፍትሄዎችን ለመስጠት የሚያስችል ዕድል ይከፍታል ተብሏል።
ይህ ታሪካዊ ክስተት በዓለም ዙሪያ በሚገኙ የሕክምና ባለሙያዎች ዘንድ ከፍተኛ አድናቆትንና ውይይቶችን እያስነሳ ሲሆን፣ ለሕክምና እድገት ትልቅ አስተዋጽኦ ያደርጋል ተብሎ ይጠበቃል።
__
ሀሳብ እና’ሳ’ፍራለን 📞
👉011-639-28-52
👉011-639-37-63
ምላሽ ይስጡ