ሐምሌ 21 ቀን 2017(መናኸሪያ ሬዲዮ) ከሰሞኑን እየጣለ ባለው ከፍተኛ ዝናብ የኦሞ ወንዝ ሞልቶ በአርብቶ አደሩ ምርትና እህል ላይ ከፍተኛ ውድመት ማድረሱን ለመናኸሪያ ሬዲዮ የገለጹት የደቡብ ኦሞ ዞን የግብርና እና አካባቢ ጥበቃ መምሪያ ሃላፊ አቶ መልኬ ከላጌ ናቸው።
የወንዝ ሙላቱ እስካሁን በሰው ህይወት ላይ ምንም አይነት ጉዳት እንዳላደረሰ የገለጹት ኃላፊው፤ ከፍተኛ የአደጋ ስጋት ያለባቸው ሶስት ስፍራዎች መለየታቸውን ተናግረዋል።
በአካባቢው የሚኖሩ የማህበረሰብ ክፍሎች ከፍተኛ ጥንቃቄ እንዲያደርጉም የግንዛቤ ማስጨበጫ ስራ እየተሰራ መሆኑን አስታውቀዋል።
ከአምናው ልምድ በመውሰድ በአከባቢው ያሉ ማህበረሰቦች እንዲነሱ የማሳሰብና አርብቶ አደሩ የአደጋ ስጋት ካለባቸው አከባቢዎች ራቅ ብሎ እርሻውን እንዲያከናውን መደረጉን ያስታወቁት ኃላፊው፤ የጉዳቱን መጠን የሚያጠኑ ባለሙያዎች ወደ ስፍራው መላካቸውን ገልጸዋል።
በቀጣይም ወንዙ ከዚህም የበለጠ ጉዳት ሊያስከትል ስለሚችል፤ የቅድመ ጥንቃቄ ስራ በትኩረት እየተሰራ ነው ብለዋል።
ከዚህ ቀደም በጎርፍ አደጋ ከቀያቸው ተፈናቅለው የነበሩት በዞንና በወረዳ አመራሮች ርብርብ ድጋፍ እየተደረገላቸው መቆየቱን ኃላፊው አስታውቀዋል፡፡
__
ሀሳብ እና’ሳ’ፍራለን 📞
👉011-639-28-52
👉011-639-37-63
ምላሽ ይስጡ