ሐምሌ 17 ቀን 2017(መናኸሪያ ሬዲዮ)23 ሚሊዮን አሜሪካውያን የቸኮሌት ወተት የሚመነጨው ከቡናማ ቀለም ካላቸው ላሞች ነው ብለው እንደሚያምኑ ተገለጸ። ይህ መረጃ ቀልድ ሳይሆን፣ በ2017 የአሜሪካ የወተት ምርቶች ኢኖቬሽን ማዕከል (Innovation Center for U.S. Dairy) ባደረገው እውነተኛ ጥናት የተገኘ ውጤት ነው ተብሏል።
ይህ የምርምር ውጤት ተመራማሪዎችን በእጅጉ አስገርሞ፣ በአሜሪካ ውስጥ የምግብ ትምህርት እጥረት እንዳለ የሚያመላክት ከባድ ውይይቶችን አስነስቷል።
እውነታው ግን፤የቸኮሌት ወተት የሚዘጋጀው ነጭ ወተት፣ ኮኮዋ እና የስኳር ንጥረ ነገሮችን በመቀላቀል ነው የተባለ ሲሆን የላሟ ቀለም ከዚህ ሂደት ጋር ምንም ግንኙነት የለውም ተብሏል፡፡
ይህ ልዩ እውነታ አስቂኝ ብቻ አይደለም፤ ይልቁንም በርካታ ሰዎች ምግብ እንዴት እንደሚመረት ከሚለው እውነታ ምን ያህል እንደተለያዩ የሚያሳይ ነው ተብሏል። በዚህም ምክንያት የትምህርት ባለሙያዎች እና የወተት ኢንዱስትሪው አካላት ከዚያን ጊዜ ጀምሮ የተሻሉ የምግብ እውቀት ማስጨበጫ ፕሮግራሞችን ለማስፋፋት እየጣሩ ይገኛሉ ተብሏል።
__
ሀሳብ እና’ሳ’ፍራለን 📞
👉011-639-28-52
👉011-639-37-63
ምላሽ ይስጡ