ሐምሌ 17 ቀን 2017(መናኸሪያ ሬዲዮ)በጃፓን የሪከን ማዕከል (RIKEN Center) እና የቶኪዮ ዩኒቨርሲቲ ተመራማሪዎች በአዲስ መልክ የተሰራ ባዮዲግሬድድ (Biodegradable) ፕላስቲክ ይፋ አድርገዋል። ይህ ፕላስቲክ በሰዓታት ውስጥ በባህር ውሃ ውስጥ ሊሟሟ የሚችል ሲሆን፣ በአፈር ውስጥ ደግሞ በ10 ቀናት ውስጥ ሙሉ በሙሉ በመከፋፈል እንደ ፎስፈረስ እና ናይትሮጅን ያሉ ንጥረ ነገሮችን በመልቀቅ የአፈርን ለምነት ይጨምራል ነው የተባለው።
ይህ አዲስ ፕላስቲክ የተሰራው ከሶዲየም ሄክሳሜታፎስፌት (sodium hexametaphosphate) እና ከጉዋኒዲኒየም-መሰረት ካላቸው ሞኖመሮች (guanidinium-based monomers) ነው ተብሏል። ሲበሰብስ የማይክሮፕላስቲክ ቅሪት የማይተው፣ መርዛማ ያልሆነ እና 91 በመቶ እንደገና ጥቅም ላይ ሊውል የሚችል ነው ተብሏል፡፡
ይህ ፈጠራ ለእርሻ ስራ የሚያገለግሉ ቁሳቁሶች ፤ የአሳ ማጥመጃ መሳሪያዎች እና ለአካባቢ ጥበቃ ተስማሚ የሆኑ ማሸጊያዎች (eco-friendly packaging) ተስማሚ ነው ተብሏል፡፡
በመሆኑም የፕላስቲክ ብክለትን ለመቀነስ እና ዘላቂነት ያለው ግብርናን ለማሳደግ ወሳኝ ሚና ይጫወታል ተብሎ ይጠበቃል ተብሏል።
ምላሽ ይስጡ