ሐምሌ 17 ቀን 2017(መናኸሪያ ሬዲዮ)ከዚህ ቀደም የወጡ አንዳንድ ህጎች ዲጂታልን ታሳቢ አድርገው የተዘጋጁ ባለመሆናቸው በዘርፉ ከፍተኛ ክፍተት መፈጠሩን የኢኖቬሽንና ቴክኖሎጂ ሚኒስቴር ለመናኸሪያ ሬዲዮ አስታውቋል።
በኢኖቬሽንና ቴክኖሎጂ ሚኒስቴር የሚኒስትሩ ከፍተኛ አማካሪ ዶክተር አብዮት ባዩ ዲጂታል ኢትዮጵያን እውን ለማድረግ ከዚህ ቀደም የወጡ እና በአዲስ መልኩ በሚዘጋጁ ህጎች ላይ መስራት ያስፈልጋል ብለዋል።
ሀገሪቱ ከሌሎች የአለም ሀገራት ጋር ተወዳዳሪ የምትሆንበት እንዲሁም የተሻለ እድገት ማስመዝገብ የምትችለው የዲጂታል ስርዓትን ተግባራዊ ስታደርግ ነው የሚሉት ዶክተር አብዮት፤ ይህ ለማሳካት የመሰረተ ልማትን ከማስፋፋት ጀምሮ የህግ ማዕቀፎችን ማሻሻል ላይ በትኩረት መስራት ይገባል ብለዋል።
የሚመለከታቸው የመንግስት ተቋማት እና ሌሎች በዘርፉ የሚሰሩ አጋር አካላት ሊሳተፉ እንደሚገባ አንስተዋል።
በ2025 ዲጂታል ኢትዮጵያን እውን ለማድረግ በተሰራው ስራ አንዳንድ የተሻሻሉ ህጎች መኖራቸውን በማስታወስ፤ በቀጣይ ሌሎቹንም መፈተሽ ይገባል ብለዋል።
የኢኖቬሽንና ቴክኖሎጂ ሚኒስቴር በ2030 ዲጂታል ኢትዮጵያን እውን ለማድረግ በሚሰራው ስራ ለዘርፉ ማነቆ የሚሆኑ ተግዳሮቶችን በመፍታት እቅዱ እንዲሳካ ሁሉም የበኩሉን ሀላፊነት መወጣት አለበት ብሏል።
__
ሀሳብ እና’ሳ’ፍራለን 📞
👉011-639-28-52
👉011-639-37-63
ምላሽ ይስጡ