ሐምሌ 16 ቀን 2017(መናኸሪያ ሬዲዮ)በገጠር እና በከተማ የሚገኙ መደበኛም ሆነ ኢ-መደበኛ ነጋዴዎች ፣አምራቾች እና ኢንተርፕራይዞች ላይ ለመጀመሪያ ጊዜ ቆጠራ እንደሚደረግ መገለጹ ይታወሳል፡፡
እስከ ሚያዚያ ወር 2018 አ.ም ድረስ ይጠናቀቃል ተብሎ የሚጠበቀው ቆጠራው በኢኮኖሚያዊ እንቅስቃሴ ላይ የተሰማሩ ግለሰቦችንም ሆነ ተቋማትን አጠቃላይ መረጃዎችን ለማደራጀት በማሰብ መሆኑን የስታስቲክስ አገልግሎት የኮሙኒኬሽን እና ህዝብ ግንኙነት ስራ አስፈጻሚ አቶ ሳፊ ገመዱ ገልጸዋል። በመላ የሃገሪቷ ክፍል ያለውን የንግድ እንቅስቃሴዎች፣የገበያ ሰንሰለቱን፣የምርት መነሻ እና መዳረሻዎች እንደሚሰበሰብ አቶ ሳፊ ተናግረዋል፡፡
በተጨማሪም በድርጅቶች ውስጥ ያሉ አስፈላጊውን የሰራተኞች ቁጥር፣የሃብት መጠን እና ምን ያክል ገቢ በስራቸው እንደሚያገኙ ጭምር የሚስበብሰበት መሆኑን አክለዋል።
በሁለት ዙር በመላ ሃገሪቱ ያሉ የንገድ ተቋማትን መረጃ ተሰብስቦ እንዲጠናቀቅ አስፈላጊው ዝግጅት እና የቅድመ ዝግጅት ስራዎች መጠናቀቃቸውን የኢትዮጲያ ስታስቲክስ አገልግሎት አመላክቷል።
ምላሽ ይስጡ