ሐምሌ 16 ቀን 2017(መናኸሪያ ሬዲዮ) በብዙዎች ዘንድ አረም ወይም ከንቱ ተብሎ የሚታሰበው የበቆሎ ፀጉር (Corn Silk)፣ ለተለያዩ የጤና እክሎች ተፈጥሯዊ መድኃኒት መሆኑ በሳይንሳዊ ጥናቶች መረጋገጡ ተገለጸ።
በተለይም ለኩላሊት ችግሮች፣ ለስኳር በሽታ እና ለሰውነት ብግነት (inflammation) ውጤታማ መፍትሄ እንደሚሆን ጥናቶች አሳይተዋል።
የበቆሎ ፀጉር እንደ ሻይ ተፈልቶ ሲጠጣ እነዚህን የጤና ችግሮች ለመከላከልም ሆነ ለማከም ይረዳል ነው የተባለው።
ሳይንቲስቶች ባደረጉት ጥናት፣ የበቆሎ ፀጉር በውስጡ ፀረ-ብግነት (anti-inflammatory)፣ የሽንት ማስወገድን የሚያግዙ (diuretic) እና የደም ስኳር መጠንን የመቆጣጠር ባህሪያት ያላቸውን ውህዶች እንደያዘ አረጋግጠዋል።
የኩላሊት ጠጠርን ለማስወገድ እና የኩላሊት ኢንፌክሽኖችን ለመቀነስ ይረዳል ተብሏል።
የደም ስኳር መጠንን ለመቆጣጠር በመርዳት የስኳር ህመምተኞች ሁኔታቸው እንዳይባባስ ድጋፍ ይሰጣል ነው የተባለው።
በሰውነት ውስጥ የሚከሰቱ የተለያዩ የብግነት ምልክቶችን በማስታገስ ህመምንና እብጠትን ለመቀነስ ያግዛልም ተብሏል።
ይህ ግኝት በተፈጥሮ የሚገኙ እፅዋትን በመጠቀም ለጤና ችግሮች መፍትሄ የመስጠትን አስፈላጊነት የሚያጎላ መሆኑ ተመላክቷል።
ይሁን እንጂ፣ ማንኛውንም የጤና ሁኔታ ለማከም የበቆሎ ፀጉርን ከመጠቀምዎ በፊት፣ በተለይም ሥር የሰደዱ በሽታዎች ካሉብዎት፣ ሁልጊዜ ከህክምና ባለሙያ ወይም ከሀኪምዎ ጋር መማከር አስፈላጊ መሆኑን ባለሙያዎች ይመክራሉ።
ምላሽ ይስጡ