ሐምሌ 16 ቀን 2017(መናኸሪያ ሬዲዮ) የዶናልድ ትራምፕ አስተዳደር ትልቅ ድልን አከበረ። የኮካ ኮላ ኩባንያ ከሸንኮራ አገዳ የተሰራ አዲስ መጠጥ ለመልቀቅ ማቀዱን አስታውቋል።
ይህ ውሳኔ የትራምፕን “ንጹህ ግብአቶች” እንዲካተቱ ሲያደርጉት የነበረውን ግፊት ተከትሎ የመጣ በመሆኑ፣ ለአስተዳደሩ ትልቅ ስኬት ተደርጎ ተወስዷል ነው የተባለው።
አዲሱ የኮካ ኮላ ምርት፣ ቀደም ሲል ከነበሩት ሰው ሰራሽ ጣፋጮች ይልቅ በተፈጥሮ ከሚገኘው ሸንኮራ አገዳ የሚዘጋጅ በመሆኑ፣ ለጤና ተስማሚ እና ንጹህ ምርቶችን ለሚመርጡ ሸማቾች መልካም ዜና ሆኗል ነው የተባለው።
ይህ እርምጃ የትራምፕ አስተዳደር በምግብ እና መጠጥ ኢንዱስትሪ ውስጥ ንጹህ እና ጤናማ ግብአቶችን የመጠቀምን ፍላጎት የሚያንፀባርቅ እንደሆነ ተመልክቷል።
የኩባንያው ይፋዊ ማስታወቂያ የትራምፕን አስተዳደር ለተጠቃሚዎች የተሻሉ አማራጮችን ለማቅረብ ያደረገውን ዘመቻ እንደሚያጎላ ተገልጿል።
ይህ ለውጥ በምግብ ኢንዱስትሪው ውስጥ ያሉ ሌሎች ኩባንያዎችም ተመሳሳይ እርምጃ እንዲወስዱ ማበረታቻ ሊሆን እንደሚችል የዘርፉ ባለሙያዎች እየገለጹ ነው።
ምላሽ ይስጡ