ሐምሌ 16 ቀን 2017(መናኸሪያ ሬዲዮ)አውስትራሊያ የባቡር ሀዲድ ጥገና ወጪን ለመቀነስ እና የአካባቢ ብክለትን ለመቀነስ የሚያስችል አዲስ ዘዴ ተግባራዊ እያደረገች መሆኑን አስታወቀች። ይህም ያገለገሉ የመኪና ጎማዎችን እንደገና ጥቅም ላይ በማዋል ወደ ባቡር ሀዲድ አስደንጋጭ መምጠጫዎች (Shock Absorbers) መለወጥን ያካትታል ነው የተባለው፡፡
ይህ አሰራር በባቡር ሀዲድ ስር የሚገጠሙትን የጎማ ንብርብሮች በመጠቀም የባቡሩን ንዝረት እና በሀዲዱ ላይ የሚደርሰውን ጫና በእጅጉ ይቀንሳል ነው የተባለው። በዚህም ምክንያት የሀዲድ መበላሸት መጠን እየቀነሰ እና በተደጋጋሚ የሚደረገው የጥገና ሥራ አስፈላጊነት እየቀነሰ መጥቷል ተብሏል፡፡
የዚህ ፕሮጀክት ትልቁ ጥቅም በየአመቱ በብዛት የሚጣሉ ያረጁ የመኪና ጎማዎች ለአካባቢ ትልቅ ፈተና ሲሆኑ፣ ወደ ጠቃሚ የግንባታ እቃዎች በመቀየር የአካባቢ ጥበቃን ይረዳል የተባለ ሲሆን በሌላ በኩል ደግሞ የባቡር ሀዲድ ጥገና ለሀገራት ከፍተኛ ወጪ የሚጠይቅ በመሆኑ፣ ይህ ዘዴ የጥገና ወጪን በመቀነስ የበጀት ጫናን ያቃልላል ተብሎለታል።
ይህ ከአውስትራሊያ የመጣው አብዮታዊ እርምጃ፣ ሌሎች ሀገራትም ዘላቂነት ያለው መፍትሄዎችን እንዲጠቀሙ ምሳሌ እንደሚሆን ይጠበቃል።
ምላሽ ይስጡ