👉የህክምና ድህረ ገጾች ስለበሽታው ምን ይላሉ?
ሐምሌ 16 ቀን 2017(መናኸሪያ ሬዲዮ) በአፍና በከንፈር አካባቢ የሚያጋጥመው ቁስለት ኸርፒስ (Herpes) በሄርፒስ ሲምፕሌክስ ቫይረስ (Herpes Simplex Virus – HSV) በመባል ይታወቃል።
ይህ ቫይረስ ሁለት ዋና አይነቶች እንዳሉት የተገለጸ ሲሆን የመጀመሪያው HSV-1 (Herpes Simplex Virus type 1) በመባል ይታወቃል ነው የተባለው።
ይህ አይነቱ ቫይረስ በአብዛኛው የአፍ ኸርፒስ ወይም ምች በመባል የሚታወቀውን የከንፈር፣ የአፍ እና የአፍንጫ አካባቢ ቁስሎችን ያስከትላል ነው የተባለው።
እነዚህም ትናንሽ፣ ፈሳሽ የቋጠሩ አረፋዎች ናቸው ተብሏል። ብዙ ጊዜ ሰዎች ገና በልጅነታቸው በዚህ ቫይረስ ሊያዙ እንደሚችሉ የተመላከተ ሲሆን መተላለፊያውም በመሳም፣ እቃዎችን በመጋራት ወይም በቀጥታ ንክኪ ሊሆን ይችላል ተብሏል።
ሁለተኛው እና ከጎልማሳ እድሜ ጀምሮ ሊከሰት የሚችለው HSV-2 (Herpes Simplex Virus type 2 የሚባል እንደሆነ የተገለጸ ሲሆን፤ ይህ አይነት ደግሞ በብዛት የብልት ኸርፒስ (Genital Herpes) በመባል የሚታወቀውን የአባላዘር ኢንፌክሽን ያስከትላል ነው የተባለው።
የሚተላለፈውም በግብረ ስጋ ግንኙነት ነው የተባለ ሲሆን በብልት አካባቢ፣ በፊንጢጣ ወይም በጭን ላይ ህመም የሚያስከትሉ፣ የሚያሳክኩ እና ፈሳሽ የቋጠሩ አረፋዎችን እንደሚያስከትል ከ WHO(World Health Organization), CDC(centers for disease control and Prevention) እና NIH(National Institutes of Health) ላይ ያገኘናቸው መረጃዎች ያመላክታሉ።
አንዴ በኸርፒስ ቫይረስ ከተያዙ፣ ቫይረሱ ሙሉ በሙሉ አይጠፋም የተባለ ሲሆን በሰውነት ውስጥ ተደብቆ ሊቀመጥ እንደሚችል እና በተለያዩ ምክንያቶች እንደ ውጥረት፣ ህመም፣ ድካም፣ የሰውነት በሽታ የመከላከል አቅም መቀነስ እንደገና ሊነቃ እና ምልክቶችን ሊያሳይ ይችላል ተብሏል።
ኸርፒስ ምልክቶች ሳይታዩበትም ሊኖር ይችላል። ነገር ግን ሲነቃ የሚያስከትላቸው ምልክቶች፤በተጎዳው አካባቢ የማቃጠል፣ የመወጠር ወይም የማሳከክ ስሜት።
ትናንሽ፣ ፈሳሽ የቋጠሩ አረፋዎች (blisters) መታየት እንደሚያስከትሉና እነዚህ አረፋዎች ሊፈነዱ፣ ቁስለት ሊሆኑ እና ቅርፊት ሊያወጡ ይችላሉ ተብሏል።
ኸርፒስ ተላላፊ ነው ተብሏል። ምልክቶች በሚታዩበት ጊዜ (አረፋዎቹ ወይም ቁስሎቹ ሲኖሩ) የመተላለፍ እድሉ በጣም ከፍተኛ መሆኑ ተመላክቷል።
ኸርፒስን ለመከላከል ምንም አይነት ፈውስ የለውም ወይም ቫይረሱን ከሰውነት ውስጥ ሙሉ በሙሉ የሚያስወግድ መድሃኒት የለም የተባለ ሲሆን ነገር ግን ምልክቶችን ለማስታገስ፣ የአረፋዎቹን የመቆየት ጊዜ ለማሳጠር እና ቫይረሱ ወደ ሌሎች የመተላለፍ እድልን ለመቀነስ የሚያግዙ ፀረ-ቫይረስ መድኃኒቶች (antiviral medications) አሉ ተብሏል።
የኸርፒስ ምልክት ከታየባችሁ ትክክለኛውን ምርመራ እና የህክምና ምክር ለማግኘት የጤና ባለሙያ ማማከር አስፈላጊ መሆኑም ተመላክቷል።
ምላሽ ይስጡ