👉ጎዳናዎችና መናፈሻዎች ያለኤሌክትሪክ ይበራሉ ነው የተባለው።
ሐምሌ 16 ቀን 2017(መናኸሪያ ሬዲዮ) ሳይንቲስቶች በጨለማ ውስጥ በራሱ የሚያበራ፣ በፈንገስ የተመሰረተ አዲስ የእንጨት ዓይነት መፍጠራቸው ተዘገበ።
ይህ አስደናቂ ግኝት የከተማ ጎዳናዎችን እና መናፈሻዎችን በተፈጥሮ ብርሃን ለማብራት የሚያስችል ሲሆን፣ ለዚህም ምንም ዓይነት ኤሌክትሪክ አያስፈልገውም ነው የተባለው።
ተመራማሪዎቹ በልዩ ሁኔታ የተሻሻሉ ፈንገሶችን በመጠቀም፣ እንጨት በራሱ ብርሃን እንዲያመነጭ የሚያስችል ቴክኖሎጂ ቀይሰዋል ተብሏል።
ይህ ማለት ለብርሃን የሚያስፈልገው ኃይል በተፈጥሮ ከእንጨቱ እና ከፈንገሱ መስተጋብር የሚመነጭ በመሆኑ፣ ባህላዊ የኤሌክትሪክ መብራቶችን የመጠቀም ፍላጎትን ያስቀራል ተብሏል።
ይህ አዲስ ፈጠራ ለአካባቢ ተስማሚ እና ዘላቂ የብርሃን አማራጮችን በማቅረብ ረገድ ከፍተኛ እምቅ አቅም እንዳለው ይታመናል።
የኤሌክትሪክ ፍጆታን በመቀነስ የኃይል ወጪዎችን ከመቆጠብ በተጨማሪ፣ የካርበን ልቀትን ለመቀነስ እና ለከተሞች ይበልጥ ተፈጥሯዊና ውብ የሆኑ የብርሃን መፍትሄዎችን ለማምጣት ያስችላል ተብሏል።
ወደፊት ይህ ቴክኖሎጂ በስፋት ጥቅም ላይ ከዋለ፣ የከተማ ገጽታን በእጅጉ ሊለውጥ እና ለአረንጓዴ የኃይል አብዮት አስተዋፅዖ ሊያደርግ ይችላል ተብሎ ይጠበቃል።
ምላሽ ይስጡ