ሐምሌ 16 ቀን 2017(መናኸሪያ ሬዲዮ)በዓለማችን ላይ የአካባቢ ብክለትን ለመቀነስ በሚደረገው ጥረት አዲስ ተስፋ የሚሰጥ ፈጠራ ይፋ ሆነ። “ጊልበርት” የተባለ ማይክሮፕላስቲኮችን ከውሃ አካላት የመሰብሰብ አቅም ያለው ሮቦቲክ ዓሳ፣ በዩኒቨርሲቲ ተማሪዎች ቡድን የተነደፈ መሆኑ ተገልጿል።
ይህ ሮቦቲክ ዓሳ በውሃ ውስጥ ተንሳፋፊ የሆኑ ጥቃቅን የፕላስቲክ ቅንጣቶችን (ማይክሮፕላስቲኮችን) ለመሰብሰብ ታስቦ የተሰራ ነው ተብሏል። የፕላስቲክ ብክለት ለባህር ውስጥ ህይወት እና በመጨረሻም ለሰው ልጅ ጤና ከባድ ስጋት እየሆነ ባለበት በዚህ ወቅት፣ እንደ ጊልበርት ያሉ ፈጠራዎች ትልቅ መፍትሄ ሊሆኑ ይችላሉ ነው የተባለው፡፡
ጊልበርት በውሃ ውስጥ የመንቀሳቀስ እና ፕላስቲኮችን በልዩ ዘዴ የመሳብ ችሎታ እንዳለው ተመራማሪዎቹ ገልጸዋል። ይህ ፕሮጀክት በዩኒቨርሲቲ ኦፍ ሰሬ (University of Surrey) ተማሪዎች ቡድን የተሰራ ሲሆን፣ ለወደፊት የውሃ አካላትን ከፕላስቲክ ብክለት ለማፅዳት በሚደረገው ጥረት ትልቅ አስተዋፅዖ እንደሚኖረው ተመላክቷል።
ይህ ተስፋ ሰጪ ቴክኖሎጂ የአካባቢ ጥበቃ ባለሙያዎች ዘንድ ከፍተኛ ትኩረት ያገኘ ሲሆን፣ ወደፊትም በስፋት ስራ ላይ ሊውል እንደሚችል እምነት ተጥሎበታል ነው የተባለው፡፡
__
ሀሳብ እና’ሳ’ፍራለን 📞
👉011-639-28-52
👉011-639-37-63
ምላሽ ይስጡ