ሐምሌ 16 ቀን 2017(መናኸሪያ ሬዲዮ)ሳይንቲስቶች መርዛማ ብረቶችን ከተመገበ በኋላ ንፁህ ወርቅ የማምረት ችሎታ ያለው ባክቴሪያ መለየታቸውን አስታወቁ። ይህ ግኝት በወርቅ ምርት ኢንዱስትሪ ውስጥ አዲስ አብዮት ሊያመጣ የሚችል እና የአካባቢ ጥበቃን በሚመለከት መልኩም ትልቅ ፋይዳ ያለው እንደሆነ ተገልጿል።
እንደ ባለሙያዎች ገለጻ፣ ይህ ባክቴሪያ መርዛማ የሆኑ ብረቶችን በመምጠጥ ወደማይጎዳ ወርቅነት የመቀየር ልዩ ተፈጥሯዊ ችሎታ አለው ነው የተባለው። ይህ ሂደት እንዴት እንደሚካሄድ ዝርዝር ጥናቶች እየተደረጉ ሲሆን፣ ወደፊት በስፋት ጥቅም ላይ እንዲውል የማድረግ እቅዶች እንዳሉ ተጠቁሟል።
ይህ ግኝት በተለይ በብረታ ብረት ማዕድን ማውጫዎች ውስጥ ያሉ መርዛማ ቆሻሻዎችን ለማጽዳት እና በተመሳሳይ ጊዜ ወርቅ ለማምረት የሚያስችል ዘላቂ መፍትሄ ሊሆን እንደሚችል የዘርፉ ባለሙያዎች እየተናገሩ ነው።
የምርምሩ ውጤቶች ለወደፊት የኢንዱስትሪ እና የአካባቢ ጥበቃ ስራዎች ወሳኝ ምዕራፍ እንደሆኑ ይታመናል።
ምላሽ ይስጡ