ሐምሌ 15 ቀን 2017(መናኸሪያ ሬዲዮ) የጃፓን አየር መንገድ (Japan Airlines – JAL) ዋና ስራ አስፈፃሚ የነበሩት ሃሩካ ኒሺማትሱ፣ የኩባንያውን ሰራተኞች ስራ ለማስቀጠል ሲሉ የራሳቸውን ደመወዝ በመቀነስ ከፓይለቶችም ያነሰ ገቢ እንዳገኙ ተገለጸ።
ይህ ታሪክ ኒሺማትሱ ሰዎችን ከትርፍ በላይ በማስቀደም ያሳዩትን አመራር የሚያሳይ ሲሆን፣ በንግዱ ዓለም ውስጥ ስነምግባር ያለው አመራር ምን ያህል ወሳኝ እንደሆነ የሚያስረዳ ምሳሌ ሆኗል ተብሏል።
ኒሺማትሱ ኩባንያው አስቸጋሪ ጊዜ ውስጥ በነበረበት ወቅት፣ ከላይ ወደ ታች የሚደረግ የመፍትሄ አሰራርን በመከተል፣ በመጀመሪያ የራሳቸውን ደመወዝ በእጅጉ ቀንሰዋል ነው የተባለው።
ይህ ውሳኔ የኩባንያውን የፋይናንስ ጫና በማቃለል እና የሰራተኞችን ስራ ከማጣት በመታደግ ትልቅ ሚና ተጫውቷል ተብሎለታል።
ስራ አስፈጻሚው ደመወዛቸውን ከነበረው ላይ ወደ $90,000 ዝቅ አድርገዋል ተብሏል። ይህም እያንዳንዱ የአየር መንገዱ ሰራተኛ ከሚያገኘው ገቢ በእጅጉ ያነሰ ነው ተብሎለታል።
ይህ ድርጊት በጃፓን ብቻ ሳይሆን በአለም አቀፍ ደረጃ አድናቆትን ያተረፈ ሲሆን፣ ለመሪዎች የኃላፊነት ስሜት እና ለሰራተኞች ያላቸውን ቁርጠኝነት አስመልክቶ ትልቅ ትምህርት ሰጥቷል ነአ የተባለው።
ኒሺማትሱ ባደረጉት ነገር፣ የአንድ ኩባንያ ስኬት በገንዘብ ትርፍ ብቻ ሳይሆን በሰራተኞቹ ደህንነት እና ሞራል ላይም የተመሰረተ መሆኑን በተግባር አሳይተዋል ነው የተባለው።
__
ሀሳብ እና’ሳ’ፍራለን 📞
👉011-639-28-52
👉011-639-37-63
ምላሽ ይስጡ