ሐምሌ 15 ቀን 2017(መናኸሪያ ሬዲዮ)ታላቁ የአኢትዮጵያ የህዳሴ ግድብ በማህበረሰቡ ተሳትፎ እንጂ የየትኛውም አለም ሀገራት ገንዘብ ያልተካተተበት መሆኑን የህዳሴ ግድብ ማስተባበሪያ ፕሮጀክት ጽ/ቤቱ ምክትል ዋና ስራ አስኪያጅ ፍቅርተ ታምር በዛሬው እለት በሰጡት ጋዜጣዊ መግለጫ አስታውቀዋል።
ግድቡ ለመጨረስ ማህበረሰቡ ከፍተኛ ተሳትፎ ያደረገበት መሆኑን በማንሳት ጽ/ቤቱ በሀገር ውስጥ እና በውጭ የሚኖሩ ኢትዮጵያውያን ድጋፍ እንዲያደርጉ ሲያስተባብር ቆይቷል።
ገቢ ከሚሰባሰብባው አማራጮች አንዱ በመሆን በከተሞች የሚሸጋገረው ገቢ ማሰባሰቢያ ዋንጫ አሁን ላይ በደቡብ ኢትዮጵያ የሚገኝ ሲሆን እስካሁ በቆየበትም 268 ሚሊዮን ብር መሰብሰቡን ገልጸዋል።
በተጠናቀቀዉ በጀት አመት ከማህበረስቡ እስከ ሰኔ ወር 2017 ዓ.ም ድረስ 1.6 ቢሊየን ብር ገቢ የተሰበሰበ ሲሆን ከዲያስፖራ ደግሞ 95 ሚሊዮን ብር መሰብሰቡን አክለዋል።
ግድቡ ከተጀመረ ጊዜ አንስቶ አጠቃላይ ከማህብረሰቡ ከ23 .6 ቢሊየን ብር ተሰብስቦ ለግድብ ግንባታ እንዲውል መደረጉን ተናግረዋል።
ማህበረሰቡ በህዳሴ ግድብ ላይ ያሳየዉን አቅም በሌሎችም ፕሮጅክቶች ላይ በማስቀጠል ለሀገሩ አስተዋጾ ማድረግ እንዳለበት አሳስበዋል፡፡
የአሜሪካዉ ፕሬዘዳንት ዶናልድ ትራንፕ ትላንት ለሶስተኛ ጊዜ የኢትዮጵያ የህዳሴ ግድብ ግንባታ በአሜሪካ የገንዘብ ድጋፍ መገንባቱን መግለጻቸዉ አይዘነጋም፡፤
__
ሀሳብ እና’ሳ’ፍራለን 📞
👉011-639-28-52
👉011-639-37-63
(https://stream.zeno.fm/yw8poig9iwtuv)
የቀጥታ ስርጭት 🔊 👉 https://zeno.fm/radio/menahria-99-1-3pw1/ (https://stream.zeno.fm/yw8poig9iwtuv)
Telegram 👉 https://t.me/menaharia_fm
ምላሽ ይስጡ