ሐምሌ 15 ቀን 2017(መናኸሪያ ሬዲዮ)በምድር ላይ ከዘመናት ሁሉ ከተመረተው ወርቅ ግማሽ ያህሉ ወይም ከዚያ በላይ የሚሆነው የተገኘው ከአንድ ቦታ ነው የተባለ ሲሆን፤ ይህም በደቡብ አፍሪካ የሚገኘው ታሪካዊው ዊትዋተርስራንድ ተፋሰስ (Witwatersrand Basin) ነው ተብሏል። ይህ ግዙፍ የወርቅ ክምችት የዓለምን የወርቅ ኢንዱስትሪ፣ የደቡብ አፍሪካን ታሪክና ኢኮኖሚ በእጅጉ የቀየረ ድንቅ የተፈጥሮ ሀብት ነው ተብሎለታል።
በዊትዋተርስራንድ የወርቅ ግኝት የተጀመረው በ19ኛው ክፍለ ዘመን መገባደጃ (በ1886 ዓ.ም አካባቢ) ሲሆን፣ ይህ ክስተት ጆሃንስበርግ የተባለችውን ከተማ ከትንሽ መንደርነት ወደ ደቡብ አፍሪካ ትልቁ የኢኮኖሚ ማዕከል እንድታድግ አድርጓታል ነው የተባለው። ወርቁ በተፋሰሱ ውስጥ ከሰሜን ምስራቅ ወደ ደቡብ ምዕራብ አቅጣጫ በሚዘረጋ ሰፊ ስፋት ላይ በተለያዩ ጥልቀቶች የተገኘ ሲሆን፣ አንዳንድ ማዕድናት እስከ 4 ኪሎ ሜትር ጥልቀት ድረስ ይዘልቃሉ ነው የተባለው።
የዊትዋተርስራንድ ተፋሰስ የጂኦሎጂያዊ አፈጣጠር እጅግ ልዩ ነው የተባለ ሲሆን ወርቁ የተከማቸው በሚሊዮኖች ለሚቆጠሩ ዓመታት በነበሩ የወንዝ ደለል ንጣፎች ውስጥ ሲሆን፣ እነዚህ ደለሎች ከጊዜ በኋላ ወደ ጠንካራ አለቶች ተለውጠው ከምድር ገጽ በታች ተቀብረዋል ነው የተባለው። ይህ ልዩ የተፈጥሮ ሂደት በዓለም ላይ ታይቶ የማይታወቅ ከፍተኛ የወርቅ ክምችት እንዲፈጠር ምክንያት ሆኗል ተብሏል፡፡
የወርቅ ማዕድናት እጅግ በጣም የበለጸጉ ከመሆናቸውም በላይ በስፋት የተዘረጉ መሆናቸው ለረጅም ጊዜ ከፍተኛ ምርት እንዲሰጡ አስችሏቸዋል ተብሏል።
__
ሀሳብ እና’ሳ’ፍራለን 📞
👉011-639-28-52
👉011-639-37-63
ምላሽ ይስጡ