👉ያለወንድ እንሽላሊቶች የዘር ፍሬ፤መጸነስና መውለድ ይችላሉ ተባለ
ሐምሌ 15 ቀን 2017(መናኸሪያ ሬዲዮ)በተፈጥሮ ህይወት ውስጥ እጅግ አስደናቂ ከሆኑ የመራቢያ ዘዴዎች አንዱ የሆነው “ፓርተኖጄኔሲስ” በተባለ ሂደት ሙሉ በሙሉ ከሴቶች ብቻ የተዋቀሩ እና ያለ ወንዶች ተሳትፎ የሚራቡ የሸምበቆ እንሽላሊት (Leiolepis) ዝርያዎች መኖራቸው ከረጅም ጊዜ በፊትም ቢሆን የሳይንስ ማህበረሰቡን ትኩረት ስቧል። ይህ ልዩ ክስተት የእንስሳትን የመራባትና የዝግመተ ለውጥ ሂደት ላይ አዲስ ግንዛቤን እየሰጠ ይገኛል ተብሏል።
ፓርተኖጄኔሲስ (Parthenogenesis) ከግሪክ ቃል የመጣ ሲሆን ትርጉሙም “ድንግል መወለድ” ማለት ነው ተብሏል። ይህ ማለት የሴት ፍጡር እንቁላል ያለ ወንድ የዘር ፍሬ (sperm) ተሳትፎ በቀጥታ ወደ ሙሉ ፍጡር የሚያድግበት የመራቢያ መንገድ ነው ተብሏል። በዚህ ሂደት የሚወለዱት ልጆች በአብዛኛው ከእናታቸው ጋር ሙሉ በሙሉ ወይም ከሞላ ጎደል ተመሳሳይ የሆነ የዘረመል ስብጥር ይኖራቸዋል ነው የተባለው፡፡
እያንዳንዱ ሴት እንሽላሊት የራሷን እንቁላል በማምረት ልጆችን ትወልዳለች፣ ለዚህም የመራቢያ ተግባር የወንድ ተሳትፎ በጭራሽ አያስፈልግም ነው የተባለው፡፡
ይህ የመራቢያ ዘዴ ለሳይንቲስቶች በርካታ ጥያቄዎችን አስነስቷል፡፡ በመጀመሪያ፣ ወሲባዊ መራባት (sexual reproduction) ከሌለ የዘረመል ልዩነት (genetic diversity) እንዴት ይጠበቃል? የሚሉ ጥያቄዎችን እያስነሳ ሲሆን፤ የዘረመል ልዩነት ለአንድ ዝርያ የአካባቢ ለውጦችን ለመቋቋም ወሳኝ ነው ተብሏል። በፓርተኖጄኔሲስ በሚራቡ ዝርያዎች ውስጥ ይህ ፈተና ቢሆንም፣ የዝግመተ ለውጥ ሂደት አንዳንድ የመላመድ ዘዴዎችን እንደፈጠረ ይታመናል ነው የተባለው።
ይህ የእንስሳት ዓለም አስገራሚ ገጽታ የሳይንስን ድንበር እየገፋ እና ስለ ህይወት ውስብስብነት ያለንን ግንዛቤ እያሰፋ ይገኛል ተብሏል።
__
ሀሳብ እና’ሳ’ፍራለን 📞
👉011-639-28-52
👉011-639-37-63
ምላሽ ይስጡ