ሐምሌ 15 ቀን 2017(መናኸሪያ ሬዲዮ)በናይጄሪያ አቡኩታ በተካሄደው የአፍሪካ ከ18 እና 20 ዓመት በታች አትሌቲክስ ሻምፒዮና ላይ የተሳተፈው የኢትዮጵያ አትሌቲክስ ልዑክ ቡድን ትላንት በሰላም ወደ ሀገሩ የገባ ሲሆን በዛሬው እለት በቼክ-ኢን ሆቴል የእውቅናና የሽልማት መርሀ-ግብር ተከናውኗል።
በዚህ ሻምፒዮና ላይ ከ44 ሀገራት የተወጣጡ 457 ሴት እና 563 ወንድ በድምሩ1,020 አትሌቶች የተፎካከሩበት ሲሆን ኢትዮጵያ 28 አትሌቶች በማሳተፍ በ2 ወርቅ፣ በ3 ብር እና በ5 ነሃስ በድምሩ 10 ሜዳልያዎችን በማስመዝገብ ሻምፒዮናውን አጠናቃለች።
የኢትዮጵያ አትሌቲክስ ፌዴሬሽን ፕሬዚዳንት ኮማንደር አትሌት ስለሺ ስህን የእንኳን ደስ አላችሁ መክፈቻ ንግግር ያደረጉ ሲሆን በቀጣይ የኢትዮጵያን ሰንደቅ አላማ በአለም አደባባይ ከፍ አድርገው የሚያውለበልቡና ስሟን የሚያስጠሩ ፤ አዳዲስ እና ተተኪ አትሌቶችን የተመለከትንበት ሻምፒዮና ነው ሲሉ ተናግረዋል።
ኢትዮጵያ በዕድሜ ተገቢነት ምርመራ ላይ የተሰራ ተግባር ለሌሎች የአፍሪካ ሀገሮች እንደ ተሞክሮ ሆኖ የታየበት ሻምፒዮና ስለመሆኑም በሽልማት መድረኩ ላይ የተነሳ ሀሳብ ነው።
ውጤቱን በዝርዝር ስንመለከት
በ5,000ሜ ሴት እርምጃ ከ18 ዓመት በታች ህይወት አምባው ወርቅ ሜዳሊያ
በ800ሜ ሴት ከ18 ዓመት በታች- ኤልሳቤጥ አማረ የወርቅ ሜዳሊያ
በ3000 ሜትር ሴቶች ከ18 ዓመት በታች -ደስታ ታደለ ብር ሜላሊያ
በ3000ሜ ሴት ከ20 ዓመት በታች -ትርሐስ ገብረሂወት ብር ሜዳሊያ
በ1500 ሜ ሴት ከ18 ዓመት በታች -ኤልሳቤጥ አማረ የብር ሜዳሊያ
በ1500 ሜ ሴት ከ18 ዓመት በታች – ደስታ ታደሰ ነሀስ ሜዳሊያ
በ3000 ሜትር ሴቶች ከ18 ዓመት በታች ብርነሽ ደሴ ነሀስ ሜዳሊያ
በ400ሜ ሴት ከ18 ዓመት -ባንቻአለም ቢክስ ነሀስ ሜዳሊያ
በ1500 ሜ ወንድ ከ18 ዓመት በታች – ሳሚኤል ገብረሃዋርያ ነሀስ ሜዳሊያ
በ800ሜ ወንድ ከ20 ዓመት በታች ሲሳይ ዓለቤ ነሀስ ሜዳሊያ ተመዝግቧል።

በሚካኤል ደጀኔ
__
ሀሳብ እና’ሳ’ፍራለን 📞
👉011-639-28-52
👉011-639-37-63
(https://stream.zeno.fm/yw8poig9iwtuv)
የቀጥታ ስርጭት 🔊 👉 https://zeno.fm/radio/menahria-99-1-3pw1/ (https://stream.zeno.fm/yw8poig9iwtuv)
Telegram 👉 https://t.me/menaharia_fm
ምላሽ ይስጡ