ሐምሌ 14 ቀን 2017(መናኸሪያ ሬዲዮ) በተያዘው በጀት አመት በአለም አቀፍ ደረጃ ድጋፍ ሲያደርጉ የነበሩ የተለያዩ ግብረሰናይ ድርጅቶች ድጋፍ መቀዛቀዝ በሴቶችና በእናቶች ላይ የሚሰሩ ሃገር በቀል ድርጅቶን እየፈተነ እንደሆነ የኢትዮጵያ የስነህዝብ ድርጅት ለመናኸሪያ ሬዲዮ አስታውቋል፡፡
ድርጅቱ በኢትዮጵያ የእናቶችን ሞት ለመቀነስ ከሚሰራው ስራ ውስጥ ቀዳሚው የቤተሰብ ምጣኔ ቢሆንም ድጋፎች መቆራረጣቸው ስራቸውን በተገቢው መንገድ እንዳይሰሩ እንቅፋት እንደሆነባቸው የድርጅቱ ምክትል ሃላፊ ዶክተር አወቀ ጣሰው ተናግረዋል፡፡
የፌደራል መንግስት የሚመድብላቸው የገንዘብ መጠን በቂ አለመሆኑ ቀዳሚው ፈተና ቢሆንም በተለያዩ የገጠሪቱ ክፍል ያሉ ዜጎች ላይ ያለው የግንዛቤ ክፍተት ድርጅቱ በአቅሙ ልክ እንዳይሰራ እንዳደረገው ዶክተር አወቀ ገልጸዋል፡፡ ሃገር በቀል ድርጅቶች በእንዲህ አይነት ወቅት ከስራቸው ሊሰናከሉ እንደማይገባ ያነሱት ዶክተር አወቀ ኢትዮጵያ በጤናው ዘርፍ እራሷን መቻል እንደሚገባት ጠቁመዋል፡፡
የፀጥታ ችግር ያለባቸው ክልሎች ለስራቸው ፈታኛ እንደሆኑ ያነሱት ምክትል ሃላፊው መንግስታዊ ያልሆኑ ድርጅቶችን በመጠቀም አገልግሎቱን ተደራሽ ለማድረግ እየተሰራ እንደሆነም ተናግረዋል፡፡
የጤና ባለሙያዎች የሌሉባቸው አካባቢዎች እንደነበሩና ድርጅቱ ባለሙያዎች በመተካት ላይ እንደሆነ ሃላፊው አንስተው አሁን ላይ የግብዓት እጥረት እንዳለም አመላክተዋል፡፡
__
ሀሳብ እና’ሳ’ፍራለን 📞
👉011-639-28-52
👉011-639-37-63
(https://stream.zeno.fm/yw8poig9iwtuv)
የቀጥታ ስርጭት 🔊 👉 https://zeno.fm/radio/menahria-99-1-3pw1/ (https://stream.zeno.fm/yw8poig9iwtuv)
Telegram 👉 https://t.me/menaharia_fm
ምላሽ ይስጡ