ሐምሌ 14 ቀን 2017(መናኸሪያ ሬዲዮ)ቻይና እስከ 1.6 ኪሎ ሜትር ያህል ርቀት ላይ የሚገኙ ክፍት መጽሐፍትን ማንበብ የሚችል አዲስ የስለላ ቴክኖሎጂ ማበልፀጓ ተዘግቧል። ይህ ቴክኖሎጂ ከፍተኛ ጥራት ባላቸው ካሜራዎች እና የላቀ ምስል ማቀናበሪያ ዘዴዎች የተደገፈ ሲሆን፣ በርቀት የሚገኙ ጽሑፎችን የማንበብ አቅም እንዳለው ነው የሚነገረው።
ይህ ቴክኖሎጂ የቻይና የክትትል አቅምን ወደ ላቀ ደረጃ እንደሚያደርሰው ስጋቶች እየተነሱ ነው።
የዚህ ቴክኖሎጂ ዝርዝር ባህሪያት እና አጠቃቀሙ በተመለከተ ተጨማሪ መረጃዎች እስካሁን ይፋ አልተደረጉም። ይሁን እንጂ፣ ይህ አዲስ ቴክኖሎጂ የግላዊነት እና የደህንነት ጉዳዮችን በተመለከተ ሰፊ ውይይት ሊያስነሳ ይችላል እየተባለ ነው።
__
ሀሳብ እና’ሳ’ፍራለን 📞
👉011-639-28-52
👉011-639-37-63
(https://stream.zeno.fm/yw8poig9iwtuv)
የቀጥታ ስርጭት 🔊 👉 https://zeno.fm/radio/menahria-99-1-3pw1/ (https://stream.zeno.fm/yw8poig9iwtuv)
Telegram 👉 https://t.me/menaharia_fm
ምላሽ ይስጡ