👉ሳይንቲስቶች ለሰው ልጅ ፍጆታ እንዲሆን እያጠኑት ነው ተብሏል
ሐምሌ 14 ቀን 2017(መናኸሪያ ሬዲዮ)በቅርብ ጊዜ የተደረገ ሳይንሳዊ ጥናት እንደሚያመለክተው፣ የአንድ የተወሰነ የምስጥ ዝርያ የሚያመርተው “ወተት” ከላም ወተት ጋር ሲነፃፀር እጅግ በጣም ከፍተኛ የሆነ የንጥረ ነገር ይዘት ያለው ሲሆን፣ ይህ ግኝት የምግብ ዋስትናን ለማረጋገጥ አዲስ ተስፋን ፈጥሯል ነው የተባለው። ሳይንቲስቶችም ይህን አስደናቂ ግኝት ለሰው ልጅ ፍጆታ የማዋል እድልን በስፋት እየመረመሩት መሆኑን አስታውቀዋል።
ፓሲፊክ ቢትል ኮክሮች (Pacific Beetle Cockroach) የተባለው ልዩ የምስጥ ዝርያ ለግልገሎቹ ዕድገት የሚያስፈልጉትን ንጥረ ነገሮች የያዘ በፕሮቲን የበለፀገ ክሪስታል ያመርታል ነው የተባለው።
እ.ኤ.አ በ2016 በህንድ በሚገኘው የስቴም ሴል ባዮሎጂ እና ተሃድሶ ህክምና ተቋም (Institute of Stem Cell Biology and Regenerative Medicine) ተመራማሪዎች ባደረጉት ጥናት፣ እነዚህ የወተት ክሪስታሎች ከላም ወተት (ወይም ከጎሽ ወተት) በሦስት እስከ አራት እጥፍ የበለጠ ኃይል ሰጪ እና ገንቢ መሆናቸውን ደርሰውበታል ተብሏል።
በውስጡ አስፈላጊ የሆኑ አሚኖ አሲዶችን፣ ከፍተኛ መጠን ያለው ፕሮቲን፣ ቅባቶች እና ስኳርን በመያዙ፣ ለሰውነት ዕድገትና ጤና ወሳኝ የሆኑ ሁሉም ንጥረ ነገሮች በተቀናጀ መልኩ እንደሚገኙበት ተመላክቷል።
የዓለም ህዝብ ቁጥር እየጨመረ በሄደ ቁጥር የምግብ ፍላጎት መጨመር እና የዘላቂነት ጥያቄዎች የአለም አቀፍ ፈተናዎች ሆነዋል። በዚህም ሳቢያ ሳይንቲስቶች ለወደፊቱ የሰው ልጅ የምግብ ፍላጎትን ለማሟላት አማራጭ እና ቀልጣፋ የምግብ ምንጮችን በማፈላለግ ላይ ናቸው ተብሏል። የምስጥ ወተትም ይህንን ክፍተት ለመሙላት ከፍተኛ አቅም እንዳለው ታምኖበታል ነው የተባለው።
ምንም እንኳን የምስጥ ወተት እጅግ ገንቢ ቢሆንም፣ ከምስጦች ላይ በቀጥታ ወተት ማጥባት (milking) ተግባራዊ ለማድረግ የማይቻል በመሆኑበምትኩ ሳይንቲስቶች የወተት ፕሮቲንን የሚያመርቱትን ጂኖች ለይተው በማውጣት፣ እነዚህን ፕሮቲኖች በቤተ ሙከራ ውስጥ እርሾን ወይም ባክቴሪያን በመጠቀም በብዛት የማምረት ዘዴዎችን እየመረመሩ መሆኑ ተነግሯል።
ይህ ቴክኖሎጂ ተፈፃሚ ከሆነ፣ የምስጥ ወተትን ለንግድ የሚያስችል ደረጃ ላይ ማድረስ ይቻላል ተብሎ ይጠበቃል ተብሏል፡፡
የምስጥ ወተት በአሁኑ ወቅት የዕለት ተዕለት የምግብ ፍጆታ አካል ባይሆንም፣ በመካሄድ ላይ ያሉ ጥናቶች እና የቴክኖሎጂ እድገቶች ከጊዜ በኋላ የፕሮቲን እጥረት ችግርን ለመቅረፍ እና ለዘላቂ የምግብ ሥርዓቶች አስተዋፅኦ የማድረግ አቅም እንዳላቸው ተመላክቷል፡፡
__
ሀሳብ እና’ሳ’ፍራለን 📞
👉011-639-28-52
👉011-639-37-63
(https://stream.zeno.fm/yw8poig9iwtuv)
የቀጥታ ስርጭት 🔊 👉 https://zeno.fm/radio/menahria-99-1-3pw1/ (https://stream.zeno.fm/yw8poig9iwtuv)
Telegram 👉 https://t.me/menaharia_fm
ምላሽ ይስጡ