ሐምሌ 14 ቀን 2017(መናኸሪያ ሬዲዮ)የጤና መድህን አገልግሎት ተጠቃሚ ሁነው የመክፍል አቅም ለሌላቸው ዜጎች መንግስት ሙሉ ወጪያቸውን መሸፈን የሚችልበት አሰራር መዘጋጀቱን የኢትዮጵያ ጤና መድህን አገልግሎት ለመናኸሪያ ሬዲዮ አስታውቋል፡፡
በ2018 በጀት አመት ገቢን መሰረት ያደረገ የክፍያ አገልግሎት እንደሚጀመር በአገልግሎቱ የአባላት አስተዳደርና ሀብት አሰባሰብ መሪ ሥራ አስፈፃሚ አቶ ጉደታ አበበ ተናግረዋል፡፡
በአገልግሎቱ ከዚህ ቀደም ሁሉም ተጠቃሚ እኩል ክፈያ ይከፍል እንደነበር ሥራ አስፈፃሚው አንስተው፤ በ2017 በጀት አመት በ738 ወረዳዎች ከከፍያ ነፃ አገልግሎት መጀመሩን አስታውቀዋል፡፡
የጤና ተቋማት ጥራት ያለው የህክምና አገልግሎት እንዲሰጡ እንዲሁም መድሃኒቶችን እንዲያሟሉ ቀድሞ የ6 ወር የቁርጥ ክፍያ በመጪው በጀት አመት እንደሚጀመርና የተጠቃሚዎች መረጃም ሙሉ በሙሉ ዲጅታላይዝድ እንደሚደረግ ተናግረዋል፡፡
የሁሉም የአባላት ዝርዝር በፆታና በስም ተለይቶ ዘመናዊ የመረጃ አያያዝ ተግባራዊ እንደሚደረግ እና አሰራሩን ማዘመን ላይ በትኩረት እየተሰራ መሆኑን አቶ ጉደታ ተናግረዋል፡፡
በመጪው በጀት አመት አሰራሩን ከማዘመን ባሻገር ሁሉም ዜጋ አገልግሎቱን የሚጠቀምበትን አሰራር መዘርጋትና አገልግሎቱ ያልተጀመረባቸው ወረዳዎች ላይ በዘመነ መንገድ አገልግሎቱን ለማስጀመር እየተሰራ መሆኑን የኢትዮጵያ ጤና መድህን አገልግሎት የአባላት አስተዳደር እና ሀብት አሰባሰብ መሪ ሥራ አስፈፃሚ አቶ ጉደታ አበበ አመላክተዋል፡፡
__
ሀሳብ እና’ሳ’ፍራለን 📞
👉011-639-28-52
👉011-639-37-63
(https://stream.zeno.fm/yw8poig9iwtuv)
የቀጥታ ስርጭት 🔊 👉 https://zeno.fm/radio/menahria-99-1-3pw1/ (https://stream.zeno.fm/yw8poig9iwtuv)
Telegram 👉 https://t.me/menaharia_fm
ምላሽ ይስጡ