👉በፈላ ጋዝ ራሱን የሚከላከል ልዩ ፍጥረት ነው ተብሎለታል
ሐምሌ 14 ቀን 2017(መናኸሪያ ሬዲዮ)በተፈጥሮ ዓለም ውስጥ በርካታ አስገራሚ ፍጥረታት ይገኛሉ። ከእነዚህም መካከል “ቦምበርድየር” (Bombardier) በመባል የሚታወቀው ጥንዚዛ አንዱ ነው። ይህ ጥንዚዛ በአስደናቂ የመከላከያ ዘዴው ሳይንቲስቶችን አስገርሟል።
የ”ቦምበርድየር” ጥንዚዛ አደጋ ሲያጋጥመው ከሰውነቱ ጫፍ ላይ 212 ዲግሪ ፋራናይት (100 ዲግሪ ሴልሲየስ) የሚደርስ ትኩስ እና ፈንጂ ጋዝ ይረጫል ነው የተባለው። ይህንን ጋዝ ለመርጨት ሁለት ኬሚካሎችን፣ ሃይድሮጅን ፔሮክሳይድ (Hydrogen Peroxide) እና ሃይድሮኩዊኖን (Hydroquinone)፣ በልዩ ክፍል ውስጥ በማዋሃድ ፈንጂ ምላሽ እንዲፈጥሩ ያደርጋል ነው የተባለው።
ጥንዚዛው በውስጡ “የፍንዳታ ክፍል” (Explosion Chamber) የሚባል አካል ያለው ሲሆን፣ በዚህ ክፍል ውስጥ ኬሚካሎቹ ሲቀላቀሉ የሚፈጠረውን ትኩስ ጋዝ በ”ስፊንክተር ማስል” (Sphincter Muscle) አማካኝነት በመቆጣጠር ወደ ውጭ ይረጫል ነው የተባለው።
ይህ አስደናቂ የተፈጥሮ መከላከያ ዘዴ ጥንዚዛው ከአዳኞች እንዲያመልጥ ያስችለዋል ተብሎለታል።
__
ሀሳብ እና’ሳ’ፍራለን 📞
👉011-639-28-52
👉011-639-37-63
(https://stream.zeno.fm/yw8poig9iwtuv)
የቀጥታ ስርጭት 🔊 👉 https://zeno.fm/radio/menahria-99-1-3pw1/ (https://stream.zeno.fm/yw8poig9iwtuv)
Telegram 👉 https://t.me/menaharia_fm
ምላሽ ይስጡ