ሐምሌ 14 ቀን 2017(መናኸሪያ ሬዲዮ) በኢንዶኔዢያ ሱላዌሲ የባህር ዳርቻ ላይ አንድ ጀልባ በእሳት ከተያያዘ በኋላ ሦስት ሰዎች ሲሞቱ፣ ከ500 በላይ የሚሆኑ ተሳፋሪዎች ግን ሕይወታቸውን ማትረፍ ችለዋል ተብሏል። የማኅበራዊ ሚዲያ ቪዲዮዎች እንደሚያሳዩት፣ እጅግ በጣም የተደናገጡ ተሳፋሪዎች ከሚነደው መርከብ ላይ ነበልባል እና ጥቁር ጭስ እየተንቦገቦገ ወደ ባህር ሲዘሉ ይታያል።
የኢንዶኔዢያ የባህር ዳርቻ ጥበቃ እንደገለጸው፣ እሁድ ዕለት ከታላውድ ደሴቶች ወረዳ ሜሎንጓኔ ወደብ ወደ ሰሜን ሱላዌሲ ግዛት ዋና ከተማ ማናዶ ሲጓዝ የነበረው KM ባርሴሎና 5 የተባለው መርከብ ላይ እሳት ከተነሳ በኋላ ተሳፋሪዎች ወደ ባህር ውስጥ ዘልለዋል ተብሏል። በማኅበራዊ ሚዲያ የተሰራጩ ፎቶዎች እና ቪዲዮዎች፣ አብዛኞቹ የሕይወት ጃኬት የለበሱ፣ የተደናገጡ ተሳፋሪዎች ወደ ባህር ውስጥ ሲዘሉ እና ብርቱካናማ ነበልባልና ጥቁር ጭስ ከሚነደው መርከብ ሲወጣ ያሳያሉ።
የማናዶ የነፍስ አድን ኤጀንሲ ያወጣው ቪዲዮ ደግሞ አንድ የባህር ዳርቻ ጥበቃ መርከብ ጥቁር ጭስ ወደሚያወጣው ጀልባ ውሃ ሲረጭ ያሳያል ነው የተባለው።
የኢንዶኔዢያ ባለሥልጣናት በመጀመሪያ አምስት ሰዎች በአደጋው መሞታቸውን ቢዘግቡም፣ በኋላ ግን በመጀመሪያ የሞቱ ተብለው ከተዘገቡት ሁለት ተሳፋሪዎች መካከል፣ ሳንባዋ በባህር ውሃ የተሞላ የሁለት ወር ሕፃን ጨምሮ፣ በሆስፒታል ውስጥ ከዳኑ በኋላ የሟቾችን ቁጥር ወደ ሦስት ዝቅ አድርገዋል ነው የተባለው፡፡
የብሔራዊ ፍለጋ እና ማዳን ኤጀንሲ ዛሬ ባወጣው መግለጫ እንዳስታወቀው፣ ቢያንስ 568 ሰዎች ከጀልባው መትረፍ ችለዋል ብሏል፡፡
በነፍስ አድን ዘመቻው አንድ የባህር ዳርቻ ጥበቃ መርከብ፣ ስድስት የነፍስ አድን መርከቦች እና በርካታ ጀልባዎች መሰማራታቸው ተዘግቧል፡፡
__
ሀሳብ እና’ሳ’ፍራለን 📞
👉011-639-28-52
👉011-639-37-63
(https://stream.zeno.fm/yw8poig9iwtuv)
የቀጥታ ስርጭት 🔊 👉 https://zeno.fm/radio/menahria-99-1-3pw1/ (https://stream.zeno.fm/yw8poig9iwtuv)
Telegram 👉 https://t.me/menaharia_fm
ምላሽ ይስጡ