👉የፈጠራ ስራ ወይስ የሩቅ ህልም?
ሐምሌ 12 ቀን 2017(መናኸሪያ ሬዲዮ)አንድ ግለሰብ የኤሌክትሪክ መኪናውን ቴስላ ሞዴል 3ን በፀሐይ ኃይል በመሙላት የቴክኖሎጂ አዲስ ምዕራፍ ከፍቷል። ይህ ፕሮጀክት ከፍርግርግ(off-grid) ውጭ የኤሌክትሪክ ተሽከርካሪዎችን ለመሙላት ያለውን እምቅ አቅም ቢያሳይም፣ ለአሁኑ የዕለት ተዕለት አጠቃቀም ተግባራዊ የሚሆንበት ደረጃ ላይ እንዳልደረሰ ተዘግቧል።
ግለሰቡ 120 ዋት የሚያመነጭ የብሉቲ (Bluetti) የፀሐይ ብርሃን ሰብሳቢ (solar panel) በቴስላ ሞዴል 3 መኪናው ጣሪያ ላይ በመገጠም፣ ይህንን የፀሐይ ኃይል ከብሉቲ AC200P ፓወር ጣቢያ ጋር በማገናኘት መኪናውን ለመሙላት ተጠቅሞበታል ነው የተባለው።
ይህ አወቃቀር በቀን ውስጥ በአማካይ 7 ማይል (በሙሉ የፀሐይ ብርሃን በሰዓት 1 ማይል) እንደሚጓዝ አስችሎታል ተብሏል። ይሁን እንጂ፣ የፀሐይ ብርሃን ሰብሳቢው ኃይል በብቃት ለመሰብሰብ በተደጋጋሚ ለፀሐይ አቅጣጫውን ማስተካከል እንደሚያስፈልግ እና በጥላ ቦታዎች ደግሞ ውጤታማነቱ በእጅጉ እንደሚቀንስ ተመላክቷል።
ይህ የፈጠራ ስራ የፀሐይ ኃይልን በመጠቀም የኤሌክትሪክ ተሽከርካሪዎችን የመሙላት የወደፊት ተስፋን የሚያሳይ ቢሆንም፣ በአሁኑ ወቅት ሰፋፊ ተጠቃሚዎችን ለመሳብ የሚያስችል ተግባራዊ ምቾት እና ኢኮኖሚያዊ አዋጭነት ላይ እንዳልደረሰ ተመላክቷል።
ለወደፊቱ የቴክኖሎጂ እድገቶች ግን ይህን ገጽታ ሊለውጡት ይችላሉም ተብሏል።
__
ሀሳብ እና’ሳ’ፍራለን 📞
👉011-639-28-52
👉011-639-37-63
ምላሽ ይስጡ