ሐምሌ 12 ቀን 2017(መናኸሪያ ሬዲዮ)የአፍሪካ ህብረት ኮሚሽን ሊቀመንበር የሆኑት ማህሙድ አሊ ዩሱፍ፣ በዛሬው ዕለት በዶሃ፣ ኳታር በተካሄደው ስነ-ስርዓት በዲሞክራቲክ ሪፐብሊክ ኮንጎ መንግስት (DRC) እና በአሊያንስ ፍሌቭ ኮንጎ/ማርች 23 ንቅናቄ (AFC/M23) መካከል የተፈረመውን የሰላም ስምምነት በደስታ እንደተቀበሉት የህብረቱ የመረጃና ኮሚዩኒኬሽን ዳይሬክቶሬት ባወጣው መግለጫ አስታወቀ።
ይህ ታሪካዊ ስምምነት በምስራቅ ኮንጎ ዲሞክራቲክ ሪፐብሊክ እና በታላላቅ ሀይቆች ክልል ውስጥ ዘላቂ ሰላም፣ ደህንነት እና መረጋጋትን ለማስፈን እየተደረጉ ባሉት ጥረቶች ውስጥ ትልቅ ምዕራፍ ተብሎ ተገልጿል።
ሊቀመንበሩ ስምምነቱ እንዲሳካ ገንቢ ሚና ለተጫወቱት አሜሪካ አስተዳደር እና ኳታር መንግስት፣ እንዲሁም ለምስራቅ አፍሪካ ህብረት (EAC) እና ለደቡብ አፍሪካ ልማት ማህበረሰብ (SADC) ምስጋና አቅርበዋል። በተለይም ለክቡር ሼኽ ታሚም ቢን ሀማድ ቢን ካሊፋ አል ታኒ፣ የኳታር መንግስት አሚር፣ በአፍሪካ ዙሪያ ሰላምን እና መረጋጋትን ለማስፈን ላደረጉት የማያቋርጥ ቁርጠኝነት እና አዎንታዊ ተሳትፎ ልዩ ምስጋና ማቅረባቸውን በመግለጫው ተመላክቷል፡፡
በተጨማሪም ሊቀመንበሩ ለሰላም እና እርቅ የአፍሪካ ህብረት አምባሳደር የሆኑትን ክቡር ጆአዎ ማኑዌል ጎንቻልቭስ ሎውሬንኮ፣ የአንጎላ ሪፐብሊክ ፕሬዝዳንት፣ እንዲሁም የተሾሙትን አስታራቂ ፋውሬ ኤሶዚምና ግናሲንግቤ፣ የቶጎሌዝ ሪፐብሊክ ፕሬዝዳንት፣ ላደረጉት የማያሰለስ ጥረት አድንቀዋል።
አፍሪካ ህብረት፣ የዲሞክራቲክ ሪፐብሊክ ኮንጎ እና የሩዋንዳ መንግስታት ላሳዩት የመግባባት፣ የቁርጠኝነት እና የፖለቲካ ፍላጎት አድናቆቱን የገለጸ ሲሆን፤ ይህ ስኬት ለክልላዊ ትብብር እና ዘላቂ ሰላም አዲስ ተስፋን እንደፈነጠቀ ተገልጿል።
የአፍሪካ ህብረት የተፈረመውን የሰላም ስምምነት በተሳካ ሁኔታ ተግባራዊ ለማድረግ እና በዲሞክራቲክ ሪፐብሊክ ኮንጎ ክልል ውስጥ ሰላምን፣ ደህንነትንና ልማትን ለማስፋፋት ከሁሉም ባለድርሻ አካላት ጋር ለመስራት ቁርጠኛ መሆኑን አስታውቋል።
__
ሀሳብ እና’ሳ’ፍራለን 📞
👉011-639-28-52
👉011-639-37-63
(https://stream.zeno.fm/yw8poig9iwtuv)
የቀጥታ ስርጭት 🔊 👉 https://zeno.fm/radio/menahria-99-1-3pw1/ (https://stream.zeno.fm/yw8poig9iwtuv)
Telegram 👉 https://t.me/menaharia_fm
ምላሽ ይስጡ