ሐምሌ 12 ቀን 2017(መናኸሪያ ሬዲዮ) በዓለም የዱር እንስሳት ስነ-ምህዳር ውስጥ የላቀ ቦታ የሚሰጠውና በአድኖ ችሎታው የሚታወቀው ነብር፣ በቀላሉ የሚታይ ነገር ግን እጅግ አስደናቂ የሆነ የአካል ክፍል አለው የተባለ ሲሆን ይኸውም ምላሱ መሆኑ ተመላክቷል።
ጥናቶች እንደሚያሳዩት የነብር ምላስ እጅግ በጣም ስለታማ በመሆኑ የተያዘውን አደን ቆዳ ሙሉ በሙሉ እስከ አጥንቱ ድረስ ማራገፍ የሚችል ልዩ ችሎታ አለው ተብሎለታል።
ይህ አዋጪ ባህሪ ነብር በምግብ ሰንሰለቱ ውስጥ ያለውን ቦታ ለማስጠበቅ የሚረዳው ቁልፍ መሣሪያ መሆኑ ተመላክቷል።
የነብር ምላስ ገጽታ በሺዎች በሚቆጠሩ ትናንሽ፣ ወደ ኋላ በተጠመዘዙና ሾጣጣ ቅርጽ ባላቸው “ፓፒሌዎች” (papillae) የተሸፈነ ነው ተብሏል።
እነዚህ ፓፒሌዎች ከሰው ጥፍር እና ፀጉር ጋር ተመሳሳይነት ባለው “ኬራቲን” (keratin) በሚባል ጠንካራ ፕሮቲን የተገነቡ ናቸው ተብሏል።
በቅርጽና በጠንካራነታቸው ምክንያት እነዚህ ፓፒሌዎች የፀጉር ብሩሽ (comb) ወይም የአሸዋ ወረቀት (sandpaper) የሚመስል ገጽታ ይሰጣሉ ተብሏል።
ነብር አድኖ ከያዘው እንስሳ ሥጋን ከአጥንት ላይ ለመንቀል፣ ፀጉርን ወይም ላባን ከቆዳ ላይ ለማስወገድ እነዚህን ፓፒሌዎች እንደ ሹል መፋቂያ ይጠቀማል ተብሏል።
የዱር እንስሳት ተመራማሪዎች እንደሚሉት፣ የነብር ምላስ ያለው ይህ ልዩ መዋቅር እና ተግባር ለዝግመተ ለውጥ ሂደት ምስክር ነው ተብሏል።
ይህ አስገራሚ ጥንካሬ ያለው ምላስ፣ ለነብር በአስቸጋሪ የዱር አከባቢ ውስጥ አድኖ የመኖር እና በቂ ምግብ የማግኘት ችሎታውን በእጅጉ ያሳድገዋል። የነብር ምላስ በእርግጥም የባዮሎጂካል ምህንድስና ድንቅ ስራ ነው ሲሉ ባለሙያዎች ይገልጻሉ።
ይህ እውነታ ስለ ነብሮች ያለንን ግንዛቤ ከፍ የሚያደርግ ከመሆኑም በላይ፣ በዱር ውስጥ የሚገኙ የእንስሳት ዝርያዎች እያንዳንዱ የአካል ክፍል ለህልውናቸው ምን ያህል ወሳኝ እንደሆነ በግልጽ ያሳያል ተብሏል።
__
ሀሳብ እና’ሳ’ፍራለን 📞
👉011-639-28-52
👉011-639-37-63
ምላሽ ይስጡ