ሐምሌ 11 ቀን 2017(መናኸሪያ ሬዲዮ) 22ኛውን ዓለም አቀፍ ጉባዔ እየተከናወነ ያለውም ተጋባዥ የሆኑ እንግዶች በተገኙበት እና በፓናል ውይይቶች ነው። በመርሀ-ግብሩም ከኢትዮጵያ ኢኮኖሚክ አሶሴሽን ማህበር የተውጣጡ ባለሙያዎች ፣ ከገንዘብ ሚኒስቴር እንዲሁም ተመራማሪዎች እና ጥሪ የተደረገላቸው እንግዶች ተገኝተዋል፡፡
ጉባዔው የተለያዩ ርዕሰ ጉዳዮች ላይ ትኩረት የሚያደርግ ሲሆን በዋናነት እንደ ሀገር ያለው የታክስ አሰባሰብ ፤ የማክሮ ኢኮኖሚ ማሻሺያ፤የእዳ መጠን እና መሰል ነገሮችን የተካተቱበት እና ለውይይት የቀረቡ መሆናቸዉ ተመላክቷል፡፡
መናኸሪያ ሬዲዮ ያነጋገራቸው የማህበሩ ከፍተኛ ተመራማሪ እና የፓርትነርሽፕ ኮሙኒኬሽን ዳይሬክተር ዶ/ር አብሌ መሃሪ በ1991 ዓ.ም ከተመሰረተዉ ጀምሮ በተለያዩ ጊዜያት የሚያካሂዳቸው ጉባዔዎች መኖራቸውን አንስተው፤ልክ እንደ አሁኑ አይነት የሚካሄዱ ጉባዔዎችን እንደ መነሻ በማየት ለጥናት እና ምርምር አጋዥ የሚሆኑ ግብዓቶች ማቅረብ የሚቻልበት መድረክ ነው ብለዋል።
አክለውም ጉባዔው ባለፉት አመታት ማህበሩ እያደረጋቸው ያሉ ክንውኖችን ማቅረብ የሚቻልበት ፤የተለያዩ የጥናትና ምርምር ዉጤቶች ይፋ የሚሆኑበት መሆኑ ተገልጻል፡፡ እየተካሄደ ባለው 22ኛው ጉባዔ ላይም ኢትዮጵያ ያደረገችውን የማክሮ ኢኮኖሚ ማሻሻያ አጠቃላይ እንቅስቃሴና ዉጤት ፣የታክስ አከፋፈል እንዲሁም ሀገሪቱ በአለም አቀፍ ደረጃም ሆነ በሀገር ውስጥ እያደረገቻቸው ያሉ ግብይቶች የሚዳሰሱበትም እንደሚሆን ጠቁመዋል፡፡
ዶክተር አብሌ ማህበሩ እያካሄዳቸው ያሉ ጉባዔዎች እና ጥናቶችን በተቻለ መልኩ ለፖሊሲ ግብዓት መሆን እንዲችሉ የተለያዩ ጥረቶች እንደሚቀጥሉ ተናግረዋል፡፡ 22ኛዉ አለም አቀፍ ጉባዔው በነገው ዕለትም እንደሚቀጥል ተገልጿል።
__
ሀሳብ እና’ሳ’ፍራለን 📞
👉011-639-28-52
👉011-639-37-63
(https://stream.zeno.fm/yw8poig9iwtuv)
የቀጥታ ስርጭት 🔊 👉 https://zeno.fm/radio/menahria-99-1-3pw1/ (https://stream.zeno.fm/yw8poig9iwtuv)
Telegram 👉 https://t.me/menaharia_fm
ምላሽ ይስጡ