ሐምሌ 11 ቀን 2017(መናኸሪያ ሬዲዮ)የ2017 ዓ.ም የ12ኛ ክፍል ሀገር አቀፍ ፈተና ውጤት ይፋ ከሆነ በኋላ ምንም ተማሪ ለማያሳልፉ 700 ያህል ት/ቤቶች ልዩ ማጠናከሪያ ስልጠና ትምህርት ሚኒስቴር እንደሚሰጥ ማስታወቁ ይታወሳል፡፡
የ12ኛ ክፍል ተማሪዎች ላይ የመልቀቂያ ፈተና ውጤት ከቅርብ ጊዜያት ወዲህ ለማሽቆልቆሉ የተማሪዎች አቅም ማነስ ብቻ አይደለም ያሉት መናኸሪያ ሬዲዮ ያነጋገራቸው የትምህርት ባለሞያዎች መሰረታዊ ችግሮች እና መፍትሄዎች ላይ ትኩረት የሚያደርግ ሰፊ ጥናት መደረግ አለበት የሚል ምክረ ሃሳባቸውን አቅርበዋል፡፡
በፈተና ላይ የሚታየው ውጤት ማሽቆልቆል እንደሃገር ሊያሳስብ የሚገባ ሲሆን በተለይም በዘንድሮው ዓመት 12ኛ ክፍል ተማሪዎችን ካስፈተኑ ትምህርት ቤቶች ውስጥ ምንም ተማሪ ለማሳልፉ ትምህርት ቤቶች ማጠናከሪያ ለመስጠት መታቀዱ መልካም ቢሆንም በትምህርት ስርዓቱ ላይ ያለውን ችግር ግን የሚፈታ አይደልም ያሉት የትምህርት ባለሙያው ፕሮፌሰር ጥሩሰው ተፈራ ናቸው። ፕሮፌሰር ጥሩሰው የትምህርት ስርዓቱ ላይ ያሉ ችግሮችን መለየት ሳይቻል በአጭር ጊዜ ማጠናከሪያ ትምህርት በመስጠት ብቻ ለውጥ አይመጣም የሚል እምነት አላቸው፡፡
ትምህርት ሚኒስቴር የማጠናከሪያ ትምህርት ለመስጠት ማስቡን የሚደግፉት ሌላኛው የትምህርት ባለሞያ ዶክተር ብርሃኑ መኮንን ለ700 ትምህርት ቤቶች ብቻ መስጠቱ ያለውን የትምህርት ዘርፍ ችግር አይፈታም ብለዋል፡፡
በተለይም ደግሞ በኢኮኖሚ በኩል ከፍተኛ የሆነ ሃብት ስለሚጠይቅ ሳይቋረት የተፈለገውን ውጤት እንዲያስገኝ በሚኒስቴር መስራያ ቤቱ ሃላፊነት በመሆኑ ግዜ ተወስዶ ጥናት ማድረግ እንደሚያስፈልግ ጠቁመዋል፡፡
ለዘንድሮው ሀገር አቀፍ ፈተና ዝግጅት ከክልል ትምህርት ቢሮዎች ጋር በመነጋገር ለተመረጡ 4መቶ ትምህርት ቤቶች የማጠናከሪያ ድጋፍ መደረጉን ትምህርት ሚኒስቴር ማስታወቁ ይታወሳል፡፡
__
ሀሳብ እና’ሳ’ፍራለን 📞
👉011-639-28-52
👉011-639-37-63
(https://stream.zeno.fm/yw8poig9iwtuv)
የቀጥታ ስርጭት 🔊 👉 https://zeno.fm/radio/menahria-99-1-3pw1/ (https://stream.zeno.fm/yw8poig9iwtuv)
Telegram 👉 https://t.me/menaharia_fm
ምላሽ ይስጡ