ሐምሌ 10 ቀን 2017(መናኸሪያ ሬዲዮ)በቻይና ከተሞች የሰውን ልጅ ጉልበት ሙሉ በሙሉ የሚተካ አዲስ የቴክኖሎጂ ፈጠራ ይፋ መሆኑ ተገለጸ። ይህ አዲስ ስርዓት፣ ሮቦቶችን በመጠቀም መኪናዎችን በራሳቸው ጊዜ ነዳጅ የሚሞሉበት ዘመናዊ የነዳጅ ማደያ ነው።
በዚህ ቴክኖሎጂ፣ አንድ ተሽከርካሪ ወደ ነዳጅ ማደያው ሲገባ፣ ሮቦት በራስ-ሰር የመኪናውን የነዳጅ መሙያ በር በመክፈት፣ ነዳጅ ከሞላ በኋላ በራሱ ይዘጋል። ይህ አጠቃላይ ሂደት ሁለት ደቂቃ ብቻ የሚወስድ ሲሆን፣ ይህም ጊዜን በእጅጉ የሚቆጥብ መሆኑ ተነግሯል።
የነዳጅ ማደያዎቹ ሙሉ በሙሉ በማሽን የሚንቀሳቀሱ በመሆናቸው የሰው ሰራተኛ በቦታው መገኘት እንደማይጠበቅበት ታውቋል። ይህ ፈጠራ የነዳጅ አሞላልን ሂደት ከማፍጠኑም በላይ፣ በሰው ልጆች ሊከሰቱ የሚችሉ ስህተቶችን ለማስቀረት እንደሚያስችል ባለሙያዎች ገልጸዋል።
ምላሽ ይስጡ