ሐምሌ 09 ቀን 2017(መናኸሪያ ሬዲዮ) ከአሁን ቀደም ለበርካታ ጊዜ መሸኛ ይዘው ለሚመጡም ተገልጋዮች አገልግሎቱ ቆሞ የነበረ ቢሆንም በዚህ አመት ከህዳር ወር ጀምሮ አገልግሎቱ መፈቀዱንና በዚህም አገልግሎቱ ከተጀመረ ወዲህ በበጀት አመቱ ከ27ሺህ በላይ መሸኛ ላመጡና መስፈርቱን ላሟሉ ተገልጋዮች ተገቢው ምላሽ እንደተሰጠ የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የሲቪል ምዝገባና የነዋሪነት አገልግሎት ኤጀንሲ የነዋሪነት አገልግሎት ዘርፍ ዳይሬክተር ተወካይ አቶ ይመኑ ሹሜ ለጣቢያችን ተናግረዋል።
በአገልግሎት አሰጣጡ ላይ መሟላት ከሚገባቸው ቅድመ መስፈርቶች ውስጥ ብሄራዊ መታወቂያን መያዝ አንዱ ነው ያሉት ተወካዩ በተጨማሪም ደንበኞች መሸኛ ይዘዉ እንዲመጡ እንደሚገደዱም ተናግረዋል፡፡ ይሄ አሰራር እንደ ከተማ ለ119ኙም ወረዳ እንደ መመሪያ ወርዶ እየተሰራበት ነው በማለትም መሸኛ ይዞ ለሚመጣ ማንኛውም ተገልጋይ ከብሄራዊ መታወቂያ በተጨማሪ ለሶስት ወራት የመጠበቅ ግዴታም እንዳለበት ተወካዩ አክለው ገልጸዋል።
በመሸኛ አገልግሎት አሰራሩ ላይ ከክልል የሚመጡት መረጃዎች እውነተኝነትን ለማረጋገጥ አዳጋች ነው ያሉት ተወካዩ ይሄም በሂደቱ ላይ እንደ ተግዳሮት የሚነሳ ዋነኛ ጉዳይ ነው ብለዋል። በመሆኑም ይህንን ክፍተት ለመሙላት ሲባል የፋይዳ ምዝገባውን እንደ ግዴታ ማስቀመጣቸውንም ነው አቶ ይመኑ የተናገሩት።
ኤጅንሲው ለሚጠይቀው የአገልግሎት ቅድመ መስፈርት በተለይ ከመሸኛ መረጃ ጋር በተገናኘ ተገልጋዮች ተገቢውን መረጃ አሟልተው መምጣት እንደሚጠበቅባቸው ተወካዩ አመላክተዋል።
__
ሀሳብ እና’ሳ’ፍራለን
👉011-639-28-52
👉011-639-37-63
(https://stream.zeno.fm/yw8poig9iwtuv)
የቀጥታ ስርጭት 👉 https://zeno.fm/radio/menahria-99-1-3pw1/ (https://stream.zeno.fm/yw8poig9iwtuv)
Telegram 👉 https://t.me/menaharia_fm
ምላሽ ይስጡ