ሐምሌ 09 ቀን 2017(መናኸሪያ ሬዲዮ)የኢትዮጵያ ደም እና ህብረ ህዋስ ባንክ አገልግሎት በመጪው አመት መቅኔ መሰብሰብ ሊጀምር እንደሆነ አገልግሎቱ ለመናኸሪያ ሬድዮ አስታውቋል፡፡
አገልግሎቱ እስካሁን ከሚሰጣቸው አገልግሎቶች በተጨማሪ ከመቅኔ የሚገኝ እስቲም ሲል ለመሰብሰብ ዝግጅቱን እንዳጠናቀቅ የአገልግሎቱ ምክትል ዋና ዳይሬክተር አቶ ሀብታሙ ታዬ ተናግረዋል፡፡
እስካሁን የመቅኔ አገልግሎት በሃገር ውስጥ መሰጠት እንዳልጀመረ የተናገሩት ዳይሬክተሩ፤ ከመቅኔ የሚገኘው እስቲም ሴል እንደ ካንሰር ላሉ ህክምናዎች እንደሚያገለግልና ታካሚዎችን ውደ ውጭ ሃገራት ከመላክ የሚያሳርፍ መሆኑን ገልፀዋል፡፡
ህክምና በሃገር ውስጥ ከአምስት ወር በኋላ ይጀመራል ያሉት አቶ ሃብታሙ የቅድመ ዝግጅት ስራዎች መጠናቀቃቸውንና ባላሙያዎችን ለማብቃት በዘርፉ ከፍተኛ ልምድና አቅም ባላቸው ሃገራት እንዲሰለጥኑ እየተደረገ መሆኑን ተናግረዋል፡፡
አገልግሎቱ ለህክምና የሚያገለግሉ ግብአቶችን በማሟላት ላይ እንደሆነና በተለይም ግብአቶችን በሃገር ውስጥ ለማምረት ከፍተኛ ስራ እየተሰራ እንደሆነ ጠቁመዋል፡፡
አገልግሎቱ ከጤና ሚኒስቴርና ከጥቁር አንበሳ ስፔሻላይዝድ ሆስፒታል ጋር በመሆን እንደሚሰጥ ዳይሬክተሩ አንስተው መንግስት በሃገር አቀፍ ደረጃ የህክምና ቱሪዝምን ለማሳደግ እየሰራ በመሆኑ በተለይ በሃገር ውስጥ ማይሰጡ የህክምና አገልግሎቶቹ በስፋት ሊጀመሩ እንደሚገባ አመላክተዋል፡፡
__
ሀሳብ እና’ሳ’ፍራለን
👉011-639-28-52
👉011-639-37-63
(https://stream.zeno.fm/yw8poig9iwtuv)
የቀጥታ ስርጭት 👉 https://zeno.fm/radio/menahria-99-1-3pw1/ (https://stream.zeno.fm/yw8poig9iwtuv)
Telegram 👉 https://t.me/menaharia_fm
ምላሽ ይስጡ