
ሐምሌ 08 ቀን 2017(መናኸሪያ ሬዲዮ)በAll england club አዘጋጅነት ሲከናወን የቆየው ተወዳጁ እና ትልቁ የሜዳ ቴኒስ ውድድር ዌምብልደን ትላንት ሲጠነመቀቅ በወንዶች የአለም ቁጥር 1ዱ ጣልያናዊው ያኒክ ሲነር ሲያሸንፍ በሴቶች ደግሞ ኢጋ ስዊያቴክ አሸንፋለች።
ያኒክ ሲነር ስፔናዊው ካርሎስ አልካራዝን የረታ ሲሎን ከወር ወይም ከ35 ቀናቶች በፊት በፈረንሳይ ሜዳ ኦፕን ቴኒስ ልቡ ተሰብሮ የነበረው ሲነር አሁን ብድሩን በመመለስ ዌምብልደንን ማሸነፍ የቻለ የመጀመሪያው ጣልያናዊ መሆን የቻለበትን አጋጣሚ ፈጥሯል።
በነ ሮጀርፌደረር እና ራፋኤል ናዳል ፤ በነጆኮቪች እና አንዲ መሪ የነበረው የቀድሞ ተወዳጅነት ያዘለ ፉክክር አሁን በትውልልድ ቅብብሎች በያኒክ ሲነር እና በካርሎስ አልካራዝ እየታየ የሚገኝ ሲሆን በትልቅ የፍፃሜ ጨዋታዎች ላይ በተደጋጋሚ እየተገናኙ አዝናኝ እና እልህ አስጨራሽ ፉክክር በማድረግ የቴኒስ ስፖርት ተወዳጅነቱ እንዲቀጥል በማድረጉ ሂደት ላይ የአምበሳውን ድርሻ እየተወጡ ይገኛሉ።
15 ሺ ደጋፊዎች የፈበታደሙበት የፍፃሜ ጨዋታ እንደ ወትሮው ከፍተኛ ትንቅንቅ የተደረገበት ሲሆን 4-6 ፣6-4 ፣ 6-4 እና 6፣4 በድምሩ 4-1 በማሸነፍ ታራካዊ ድሕ ተጎናፆፏል።
ስፔናዊው አልካራዝ ከዚ በፊት ከያኒክ ሲነር ጋር ያደረጋቸውን 4 ጨዋታዎች በሙሉ ያሸነፈ ቢሆንም ትላንት እጁን ለመስጠት ተገዷል። ሲነር ከ5 ሳምንት በፊት በታሪክ ረጅም ሰአት የፈጀው የሮላንድ ጌሮስ የፈረንሳይ ሜዳ ኦፕን ቴኒስ የፍፃሜ ውድድር በስፔናዊው ተስፈኛ የሜዳ ቴኒስ ተወዳዳሪ ካርሎስ አልካራዝ አሸናፊነት መጠናቀቁ የሚታወስ ነው።
ስፔናዊው አልካሪዝ ድል ያደረገበት መንገድ ብዙዎችን ያስገረመ እንደነበር የሚታወስ ነው። በፈረንሳይ ቀዩ አፈር ላይ የሚደረገው ብቸኛው አመታዊ የሮላንድ ጌሮስ የሜዳ ኦፕን ቴኒስ ውድድር ላይ ድራማዊ በሆነ መልኩ ወደ ጨዋታው በመመለስ ማለትም የመጀመሪያ ሁለት ሰርቦችን እንዲሁም ዙሮቹን 6-4 እና 7-6 በመሸነፍ 2-0 እየተመራ ቢጀምርም ቀጣዮቹን 3 ዙሮች ግን 7-6 ፤ 7-6 ፤ 10-2 በድምሩ 3-2 በማሸነፍ ነበር ታሪካዊ ድል ያስመዘገበው።
ያንን ተከትሎ ሲነር ያጋጠመው ሽንፈት በስነ ልቦናም እንደጎዳው ተናግሮ እንደነበር የሚቺወስ ነው። ዌምበልደን ላይ ግን ስፔናዊውን አልካራዝን 4-1 በመርታት ዋንጫዋን ከፍ አድርጎ ስሟል። ህልሜን እውን እያደረኩ ነው ሲል የአለም ቁጥር 1ዱ ያኒክ ሲነር ተናግሯል።
በሴቶችም የአለም ቁጥር 1ዷ ፖላንዳዊቷ ኢጋ ስዊያቴክ አሜሪካዊቷን አማንዳ አንሲሞቫን ፍፁም የበላይነት በመውሰድ 6-0 እና 6-0 በድምሩ 2-0 በማሸነፍ አሸናፊ መሎኗ ተረጋግጧል። ኢጋ ስዊያቴክ በፍፃሜው ምንም እድል ሳትሰጥ ሙሉ ሰርቦቿን በተሳካ መልኩ በመሰረብ ብዙ ሳትቸገር ነው ተጋጣሚዋን ያሸነፈችው ይህም በፍፃሜው ጨዋታ ሲያጋጥም ከ1911 በኋላ ለመጀመሪያ ጊዜ ያደርገዋል።
አሸናፊዎቹ 3 ሚሊዮን ፓውንድ እንዲሁም በፍፃሜው የተረቱት እና 2ኛ ደረጃን ይዘው ያጠናቀቁ የቴኒስ ተወዳዳሪዎች ደግሞ 1.5 ሚሊዮን ፓውንድ የገንዘብ ሸልማት የሚያገኙ ይሆናል።

__
ሀሳብ እና’ሳ’ፍራለን
👉011-639-28-52
👉011-639-37-63
(https://stream.zeno.fm/yw8poig9iwtuv)
የቀጥታ ስርጭት 👉 https://zeno.fm/radio/menahria-99-1-3pw1/ (https://stream.zeno.fm/yw8poig9iwtuv)
Telegram 👉 https://t.me/menaharia_fm
ምላሽ ይስጡ